[go: up one dir, main page]

0% found this document useful (0 votes)
101 views25 pages

Working Paper 1 Amharic

This document provides an overview of a research project aimed at addressing domestic violence in Ethiopia, Eritrea, and the UK. The project will: 1) Examine the role of faith and spirituality in deterring domestic violence by engaging with survivors, perpetrators, and faith leaders. 2) Collaborate with partners in Ethiopia and Eritrea to conduct additional research and trainings. 3) Engage stakeholders in the two countries to support implementation and share findings.

Uploaded by

antea.290
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd
0% found this document useful (0 votes)
101 views25 pages

Working Paper 1 Amharic

This document provides an overview of a research project aimed at addressing domestic violence in Ethiopia, Eritrea, and the UK. The project will: 1) Examine the role of faith and spirituality in deterring domestic violence by engaging with survivors, perpetrators, and faith leaders. 2) Collaborate with partners in Ethiopia and Eritrea to conduct additional research and trainings. 3) Engage stakeholders in the two countries to support implementation and share findings.

Uploaded by

antea.290
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd
You are on page 1/ 25

ለኦርቶዶክስ ጋብቻ መመሪያ

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰባት ስብከቶች ስለ ወንድ እና ሴት፡የትዳር ሕይወትና የትዳር ላይ ጥቃት

ጸሐፊ፡ ዶ/ር ሮሚና ኢስትራቲ (Dr Romina Istratii)


ተርጓሚዎች፡ ኤልያስ ገብረሥላሴ (Elias Gebrselassie) እና ፍሬሰንበት ገ/ዮሐንስ አድሃኖም (Fresenbet
Gebreyohanns Adhanom)

የትግበራ ጽሑፍ 1 (አማርኛ)


ጥር 2013
ተከታታይ የትግበራ ጽሑፍ

ይሄ ተከታታይ የጥናት ጽሑፍ የታተመው በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ሃይማኖታዊ-ባሕላዊ መነሾ ያላቸው የቤት
ውስጥ ጥቃቶች ቅነሳን ለማሳደግ እና ለማጠናከር የተቋቋመው ‹ድልድል› የሚለው ፕሮጀክት አካል ሆኖ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የተሠራው በለንደን
በሚገኘው የSOAS University of London ውስጥ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ በጀትም ለመጀመርያዎቹ አራት ዓመታት የተሸፈነው የዩናይትድ
ኪንግደም UK Research and Innovation (Future Leaders Fellowship, Grant Ref: MR/T043350/1) የወደፊት
መሪዎች ኅብረት ‹ለኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ለዩናይትድ ኪንግደም ዓይነተኛ በሆነው አቀራረብ፡ የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመከላከል
ሃይማኖታዊ ጥናቶችን፣ ጾታና ብልጽግና እና የሕዝብ ጤንነትን ማሰናሰል› በሚል (“Bridging religious studies, gender &
development and public health to address domestic violence: A novel approach for Ethiopia, Eritrea
and the UK”) ፕሮግራሙ ውስጥ ሲሆን የተደገፈው ደግሞ ‹ሃይማኖት፣ ንቃተ ሕሊና እና ጥቃት የመፈጸም ጠባይ፡ እምነትና መንፈሳዊነት
በጋብቻ ውስጥ የሚኖሩ ጥቃቶችን ለማስቆም ያላቸውን ሚና መረዳት› ለሚል የምርምር ፕሮጀክት (“Religion, conscience and
abusive behaviour: Understanding the role of faith and spirituality in the deterrence of intimate
partner violence in rural Ethiopia”) ከHarry Frank Guggenheim ፋውንዴሽን በ2019 (እ.ኤ.አ) በተገኘ የጥናት በጀት
ነው፡፡
ፕሮጀክቱ የቤት ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል ከየቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች ወይም ተራፊዎች እና ጥቃት ፈጻሚዎች ሃይማኖታዊ-ባሕላዊ
የእምነት መንገድ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀራረብ እና ይሄም የቤት ውስጥ ጥቃትን ለማስቆም ወይም ለማሳለጥ ከጾታ፣ ከቁስ እና ሥነ ልቦናዊ
መለኪያዎች ጋር እንዴት እንደሚቆራኝ በመረዳት ከቅኝ ከተገዛ አስተሳሰብ1 ነጻ የማውጣት መንገድን (decolonial approach)
ይከተላል፡፡ ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተባባሪዎች እና የገጠርና የከተማ ነዋሪዎች ጋር በመሥራት አዲስ የጥናት እና ተጽእኖ የማሳደር
መንገድን ለማምጣት እና በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙና የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ የሆኑ አናሳ ማኅበረሰቦችንና ስደተኞችን ለማዋሐድና
በተሻለ መንገድ ለመደገፍ እውቀትን ከሁለቱ ሀገራት ለመጠቀም የሚያልም ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ጥናትን፣ ማነቃቃትን፣ የእውቀት ልውውጥን እና
የማኅበረሰብ አሳታፊ እንቅስቃሴዎችን፣ ከአጋሮች፣ ባለ ድርሻ አካላት እና ማኅበረሰብ ጋር አብሮ መሥራትን በሦስቱ አገራት ከሚከተሉት
ጉዳዮች አንጻር ይተገብራል፡

ሀ) በቀሳውስትና በነገረ መለኮት ደቀመዛሙርት ዘንድ የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎችን/ተራፊዎችን እና ፈጻሚዎችን በተመለከተ ያለውን
ዝግጁነት ማሻሻል፡
ለ) ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚደረግባቸው ሀገራት ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ጥቃት ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት
ሃይማኖታዊ-ባሕላዊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረታቸው እንዲጨምር፡
ሐ) ለሃይማኖታዊ-ባሕላዊ ኅብረ ብሔራዊ ሕዝብ ትኩረት የሚለግስ እና ምላሽ የሚሰጥ የውስጥ ጥቃት መከላከልን እና ተጠቂዎችንና
አጥቂዎችን2 የሚደግፍ አሠራርን ማበልጸግ እና
መ) ለሁሉም የቡድን አባላት፣ የፕሮጀክት አጋሮች እና ተሳታፊዎች ዕድገትና ብልጽግና የጋራ ምርምር ቡድን መመሥረት እና ዕድሎችን
ማመቻቸት፡፡

ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ ዘንድ በጋብቻ ውስጥ ያለ ጥቃትን
በተመለከተ በተሠራ የጥናት ምርምር ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ ጥናቱ የምእመናንን ሕይወት፣ በጾታዊ መመዘኛዎች እና ልማዶች መካከል ያለውን
ግንኙነት እና በዚህ ሃይማኖተኛ ማኅበረሰብ ውስጥ በጋብቻ ውስጥ የሚኖር ጥቃት በመቀጠሉ እና በመገታቱ መካከል ያለውን ውስብስብ
ግንኙነት ከመረዳት አንጻር የእምነትን እና የሃይማኖት ልምምድ ያላቸውን ወሳኝነት አሳይቷል፡፡ እምነት የጥቃት ፈጻሚነትን ጠባይ እና በጋብቻ
ውስጥ ከሚኖር ጥቃት ጋር በተያያዘ ያሉ ልማዶችን ለመከላከል ወይም ለማስቆም ውስብስብ በሆነ መንገድ ለንጽጽር በቀረበበት ሁኔታ ጥናቱ
በነገረ መለኮት እና ባሕላዊ አረዳድ መካከል ያለውን ወሳኝ የሆነ ውጥረት ገልጧል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ቀሳውስትና የነገረ መለኮት ሊቃውንት፣ የመንግሥት አካላት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል ባለድርሻ አካላት

1
ከአስተሳሰብ ቅኝ ግዛት፡፡
2
የቤት ውስጥ ጥቃት ፈጻሚዎችን ችግራቸውን ተረድቶ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ፡፡
በምእመናን የጋብቻ ሕይወት ውስጥ እምነትና የሃይማኖት ልምምድ ያላቸውን ውስብስብ ሚና፣ በጋብቻ ውስጥ የሚኖር ጥልን
ለማስታረቅ ቀሳውስት የሚከተሉትን መንገድ በተመለከተ እና ችግሩን ለመቅረፍ ነገረ መለኮትና የኖላዊነት አገልግሎት እንዴት በአግባቡ
ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ለማስገንዘብ በሚደረግ ጥረት ይሄ የተከታታይ የትግበራ ጽሑፍ የዚህን የተጠናቀቀ የጥናት ውጤት ዋና
ዋና ግኝቶች ለብዙሀኑ ለማድረስ ያልማል፡፡ እንዲሁም አግባብነት ያላቸውን ሥነ-መለኮታዊ ሀብቶች በማደራጀትና በማሰራጨት
የሥርዓተ-ፆታ ነክ ጉዳዮችን እና የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለማስተማር የሃይማኖት አባቶችን ዝግጁነት ለማሻሻል ያለመ ነው ፡፡

የማጣቀሻ ጥቆማ
ሮሚና ኢስትራቲ (Romina Istratii) (ጥር 2013) ‹ለኦርቶዶክስ ጋብቻ መመሪያ፣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰባት ስብከቶች ስለ
ወንድ እና ሴት፡የትዳር ሕይወትና የትዳር ላይ ጥቃትትርጉም›። ትርጉም በኤልያስ ገብረሥላሴ (Elias Gebrselassie) እና ፍሬሰንበት
ገ/ዮሐንስ አድሃኖም (Fresenbet Gebreyohanns Adhanom)፡፡ የትግበራ ጽሑፍ 1 (አማርኛ). Project dldl/ድልድል:
Bridging religious studies, gender & development and public health to address domestic violence in
religious communities. SOAS University of London.
የቅጂ መብት
ከዚህ ፕሮጀክት የሚወጡ ግኝቶች ሁሉ የታተሙት በ UKRI Open Access ሕግ መሠረት እና እውቀትን ለሁሉ ለማካፈል ፕሮጀክቱ
ካለበት ግዴታ መነሾ ነው፡፡ ሁሉም ግኝቶች የታተሙት በ Creative Commons Attribution NonCommercial (CC BY-NC
4.0) International Licence, https://creativecommons.org/licenses/by-nc/4.0/ ነው፡፡
ይሄ ጽሑፍ የተወሰደው ‹ከሴቶች እኩልነት መብት ተከራካሪ ‘የጥርጣሬ ስብከት’ ባሻገር ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ወንድና ሴት ግንኙነት
ትርጓሜ ፣ ትዳርና የትዳር ላይ ጥቃት ከኦርቶዶክስ አረዳድ አንጻር” ከሚለው የሮሚና ኢስትራቲ (Romina Istratii) ጽሑፍ ነው።
ይህ ትክክለኛ ማመቻቸት በመጀመሪያ በኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ዶግማ መድረክ ላይ የታተመ ሲሆን ከመጀመሪያው አሳታሚ ፈቃድ ጋር
ይራባል ፡፡ ከዋናው ጋር ያለው አገናኝ እዚህ ይገኛል:
https://www.oodegr.com/amharic/marriage/chrysostom_conjugal_relations.htm

ምስጋና
የፊት ገጹን እና የተከታታይ ጽሑፍ ሥራውን የሄዲንግ ፔፐር ዓርማ ስለሠራልን በአዲስ አበባ ከሚገኘው ከDDN Advertising አቶ
ዳንኤል ደስታን (Daniel Desta) እናመሰግናለን፡፡
መግቢያ
አንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊት እና ሐዋርያዊት በሚሉ ቅጽሎች የምትጠራው ቅድስት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የታሪኳ ሥረ-
መሠረት ሐዋርያት የበዓለ አምሳ ዕለት የተቀበሉት መለኮታዊ መገለጥ ነው፡፡ ይህም ኦርቶዶክሳዊ መገለጥ እስካሁን ድረስ
ኦርቶዶክሳዊያን በሚገኙባቸው በመካከለኛው ምሥራቅ፣ ታናሽ እስያ፣ ሜዲትራንያን አውሮፓ፣ አፍሪቃ እና ሕንድ በሐዋርያት
እና በተከታዮቻቸው አማካኝነት ሊሰራጭ ችሏል፡፡ በቀደሙት ዘመናት ውስጥ ክርስትና በሮም ይፋዊ የመንግሥት ሃይማኖት
እስከሆነበት ወቅት ድረስ ክርስቲያኖች በሮማውያን ቄሳሮች ከፍተኛ በደል ይደርስባቸው ነበር፡፡ ምንም ስንኳ እነዚህ ቀደምት
ክርስቲኖች በአጠቃላይ የአንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊት እና ሐዋርያዊት የሆነችው ቤተክርስቲያን አካል የነበሩ ቢሆንም የተለያዩ
ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ እና ነገረ-መለኮታዊ ሁኔታዎች በምሥራቃውያን እና ምዕራባውያን ክርስቲያኖች መካከል መከፋፈልን
አስከትለዋል፡፡

በወቅቱ የተከሰቱ የተለያዩ ፖለቲካዊ ኩነቶች የምዕራቧ ቤተክርስቲያን በአስተምህሮ እና ነገረ-መለኮታዊ ጉዳዮች ላይ ራሷን
እንድትለይ [ተለይታ እንድትወጣ] አድርጓታል፡፡ ይህም ደግሞ በዐሥራ አንደኛው መቶ ክ/ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ
ለተፈጠረው ክፍፍል ምክንያት ሆኗል3፡፡ ምሥራቃውያን የቤተክርስቲያን አባቶች [ኦርቶዶክሳዊያን አባቶች] አዳዲስ
አስተምህሮዎችን ሳይጨምሩ፤ ነገር ግን በግሪክ ቋንቋ የተጻፉ ጥንታዊ መዛግብቶች ላይ በመመርኮዝ እና የጥንታዊቷን
ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የነገረ-ድኅነት መልእክት በሚገልጽ መልኩ ነገረ መለኮታዊ አስተምህሮውን ለመረዳት የሚያስችለውን
ፍልስፍናዊ መዋቅር አስተካክለዋል፡፡ በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን አረዳድ መሠረት የእነርሱ ሥራ ምድራዊ የአእምሮ ፈጠራ እና
የሥነ-አመክንዮ ፍልስፍና ውጤት ሳይሆን ከምናኔ4 እና አብርሆት [ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ መገለጥ] የመነጨ ነገረ-መለኮታዊ
አስተምህሮ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ [በግሪኩ ‹ክሪሶስቶሞስ› ተብሎ ይጠራል፤ ትርጉሙም አፈ-ወርቅ ማለት ነው]
ከእነዚህ ኦርቶዶክሳዊ አባቶች መካከል እጅግ የታወቀ የነገረ-መለኮት ሊቅ እና ቅዱስ አባት ነው፡፡5

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተወለደው የሮም ርዕሰ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ ሲሆን ጊዜውም በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን
አጋማሽ ነው፡፡ በወቅቱ ዝነኛ ከነበረው የንግግር ጥበብ መምህር ሊባኒዮስ ሥር ፍልስፍናን ቢያጠናም በመጨረሻ ግን ወደ
ኦርቶዶክሳዊነት በመመለስ ለተወሰነ ጊዜ የምናኔ ሕይወት ኖሯል፡፡ በቅስና ማዕርግ በአንጾኪያ ካቴድራል ሲያገለግል ከቆየ በኋላ
የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ መሆን ችሏል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ብዙ ስብከቶችን የሰበከ ሲሆን፤ በእነዚህም ስብከቶቹ ውስጥ
የሐዋርያቱን ትምህርት፤ በተለይም ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ክርስትና ለመጡ የመጀመሪያ መቶ ክፍለዘመን
ምዕመናን የጻፋቸውን መልእክታት በሚገባ አብራርቶ ተርጉሟል፡፡6 ትርጓሜዎቹም በአንጾኪያ ከተማ7 ውስጥ በመንሰራፋት
ላይ የነበረውን ዓለማዊነት እና ሴሰኝነት በመዋጋት የምዕመናኑንም መንፈሳዊ ሕይወት በሐዋርያዊ ትምህርት ለማሻሻል ያለሙ
ነበሩ፡፡

3
ቀሲስ ጆን ሮማኒዴስ እንደገለጹት ከሆነ ይህ ክፍፍል የተከሰተው በምዕራብ እና ምሥራቅ ክርስቲያኖች መካከል ሳይሆን ይልቁንም በምሥራቅ ሮማኒያ
እና ለፖለቲካ ጥቅማቸው ሲሉ የቀደምት ቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ የበረዙት የሮማ ግዛት ገዢዎች መካከል ነው፡፡ ይህንን ምንጭ ይመልከቱ፡-
Ιωάννης Ρωμανίδης, Ρωμηοσύνη Ρωμανία Ρούμελη (Εκδόσεις Πουρνάρας Παναγιώτης, Θεσσαλονίκη, 1975).
4
ἄσκησις’; ወደ አማርኛ ቋንቋ ሲመለስ ‹ገቢር፣ ልምድ፣ ተግባር፣ ልምምድ› የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡
5
የግሪኩ ስንክሳር እንደሚገልጸው ከሆነ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 804 ድርሳኖች ከመጥፋት ተርፈዋል፡፡ ይህንን ምንጭ ይመልከቱ፡- Ορθόδοξος
Συναξαριστής, «Άγιος Ιωάννης ο Χρυσόστομος Αρχιεπίσκοπος Κωνσταντινούπολης»,
http://www.saint.gr/3021/saint.aspx
6
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ጳውሎስ የተጻፉ አሥራ አራት መልእክታትን ትቀበላለች፡፡ እነዚህም፡- ሮሜ፣ አንደኛ/ሁለተኛ ቆሮንጦስ፣ ገላትያ፣
ኤፌሶን፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆላስይስ፣ አንደኛ/ሁለተኛ ተሰሎንቄ፣ አንደኛ/ሁለተኛ ጢሞቲዎስ፣ ቲቶ፣ ፊልሞና እና ዕብራውያን ናቸው፡፡ ከኢነዚህ ውስጥ
አሥራ ሦስቱ ስሙን ሲጠቅሱ አንዱ ግን (ዕብራውያን) ስሙን አይጠቅስም፡፡ ዘመናዊ ጥናት ከእነዚህ መልእክታት ውስጥ የተወሰኑት በጳውሎስ
የመጻፋቸውን ነገር ይጠራጠራል፡፡
7
ዘመናዊ ሊቃውንት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተለያዩ ተግሳጾች በየት ቦታ እንደተነገሩ አይስማሙም፡፡ ሆኖም ግን ብዙዎቹ ተግሳጾቹ በአንጾክያ ከተማ
የተነገሩ መሆናቸው ላይ በብዛት ስምምነት አለ፡፡
ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰባት ስብከቶች የተውጣጣ ሲሆን፤ በወንድ እና ሴት የጋብቻ ሕይወት ላይ
ያጠነጥናል፡፡ ስብከቶቹንም በምልከታ እና ልምድ በዳበረ ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ (ፍሮኒማ)8 ለመመልከት ሙከራ ተደርጓል፡
፡ ዓላማውም የቤተክርስቲያን አባቶች አስተምህሮን ለምዕመናን ነባራዊ ሁኔታዎች የበለጠ በማቅረብ ስለ ኦርቶዶክሳዊ እምነት
ያላቸውን አረዳድ ከፍ ማድረግ ነው፡፡ የዚህ ጥናት ጸሐፊም የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች ጠንካራ የሆነ ባህላዊ
መሠረት ባላቸው የኦርቶዶክስ ማኅበረሰቦች ውስጥ ከሴቶች እና ትዳር ጋር ተያይዞ ያለውን መጥፎ ልማድ ለመቅረፍ ወሳኝ
መሆኑን ታምናለች፡፡

ይህን መሰል ተግባራት ጠንካራ ባህላዊ መሠረት ባላቸው የኦርቶዶክስ ማኅበረሰቦች ውስጥ የተለመዱ ሲሆኑ፤ የኦርቶዶክስ ነገረ-
መለኮታዊ አስተምህሮዎችን በአግባቡ ካለመረዳት እና በእምነቱ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸውን ተግባራት በተመለከተ ወደ ባህላዊ
እና ማኅበረሰባዊ እይታዎች ከማዘንበል ሊመነጭም ይችላል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ አስተሳሰቦች በቤተክርስቲያን ውስጥ
ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ላይ በሚገኙ ካህናት እና አገልጋዮች መካከል ተገቢውን የትርጓሜ ዘይቤ ባልተከተለ መልኩ ስለ
ወንድ እና ሴት የጋብቻ ጥምር ግንኙነት በሚደረግ ውይይት ወይም ትምህርት በሕዝቡ ዘንድ ጠንካራ ቦታ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ለአብነት ያህል ቤተሰብን ከመበታተን በማዳን ወይንም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ጊዜ ይቅርታን ተመራጭ በማድረግ ላይ ያተኮረ
ትምህርት በባሎቻቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሚስቶች ሁኔታዎችን በዝምታ እንዲያልፉ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ የዚህ ጽሑፍ
ዓላማም በወንድ እና ሴት የጋብቻ ጥምር ግንኙነት ዙሪያ በኦርቶዶክስ ምዕመናን እና ካህናት ዘንድ ሊኖሩ የሚችሉ የተሳሳቱ
አመለካከቶችን መቅረፍ እና በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ መልካም ያልሆኑ ባህላዊ እና ማኅበረሰባዊ አስተሳሰቦችን መቀልበስ ነው፡፡

የባህል መሸርሸር እና የእምነት መበረዝ


በታሪክ ውስጥ ስንመለከት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስቀድመው በአንድ ቦታ ከነበሩ ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓቶች
ጋር ጥንቃቄ የተሞላበት ግንኙነት መሥርታ፤ በዚህም ውስጥ ኦርቶዶክሳዊነት ቀድመው ከነበሩት ሥርዓቶች ጋር ሲነጻጸር
ያለውን ሁለንተናዊ ብልጫ እና በአዳዲስ አማኞችም ዘንድ እውነተኛውን የክርስትና መልእክት በተገቢው መንገድ ለማስረጽ
ባለመ ሁኔታ ውስጥ ወንጌልን ለማሰራጨት ብዙ ሠርታለች፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች እንዲያውም፤ የአካባቢው ቀደምት አካሄድ
የክርስትና መልእክትን የማይጋፋ ሆኖ ከተገኘ ወይንም ደግሞ ቤተክርስቲያኒቷ ለአዳዲስ አማኒያን አስቸጋሪ ሁኔታዎችን
ላለመፍጠር ስትል ነባር ሥርዓቶችን አቅፎ የመጓዝ አካሄድን የተጠቀመችበት ሁኔታ አለ9፡፡ በዚህም ምክንያት አስቀድመው
የነበሩ ማኅበረሰባዊ አወቃቀሮች በክርስትና ሳይዋጡ አብረው መጓዝ ችለዋል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች እና ማኅበረሰቦች
ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶች ነባር እሳቤዎቹን ይገነዘቧቸው የነበረ ሲሆን አላስፈላጊ የሆኑትንም በግልጽ ይኮንኑ
ነበር፡፡ ለዚህም እንደ አብነት የሚጠቀሰው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባርነትን የኮነነበት መንገድ ነው10፡፡

8
«φρόνημα» የሚለው ቃል ‹ንቃተ ሕሊና› የሚል ትርጉምን ሊይዝ ይችላል፡፡ የግሪኩ ቃል እንደሚገልጸው ከሆነ ፍሮኒማ ኦርቶዶክሳዊ እምነትን
በተግባር ከመኖር የሚመነጭ እይታ ነው፡፡ እንዲህ የተባለበት ምክንያት በጥናቱ ውስጥ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
9
ይህ አካሄድ የሚታየው ቅዱስ ጳውሎስ ‹ለማይታወቅ አምላክ› በሚል የተጻፈውን የግሪክ ጽሑፍ መሠረት አድርጎ አቴናውያንን ለክርስትና ሲያስተዋውቅ
ነው፡፡(ሐዋ 17፡23)
10
እዚህ ጋር ነባቤ መለኮት ቅዱስ ጎርጎሬዎስን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እርሱም ለዘማዊ ሴት ቅጣት በማዘዝ ዘማዊ የሆነ ወንድን ግን ችላ የሚለውን ሕግ
ተመልክቶ እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡- «Τι δήποτε γαρ το μεν θήλυ εκόλασαν, το δε άρρεν επέτρεψαν; Και γυνή μεν κακώς
βουλευσαμένη περί κοίτην ανδρός μοιχάται και πικρά εντεύθεν τα των νόμων επιτίμια, ανήρ δε καταπορνεύων
γυναικός ανεύθυνος; Ου δέχομαι ταύτην την νομοθεσίαν, ουκ επαινώ την συνήθειαν. Άνδρες ήσαν οι
νομοθετούντες, διά τούτο κατά γυναικών η νομοθεσία.» ይህንን ስንተረጉመውም ‹‹ሴቷን የሚቀጧት ወንዱን ግን ይቅር የሚሉት
ስለምንድር ነው; ሴቲቷ ዘማዊ በመሆን የመኝታን ክብር ስታረክስ በከባድ ቅጣት ትቀጣለች፡፡ ወንዱ ግን ከሌሎች ሴቶች ጋር ሲሄድ የማይቀጣው
ስለምንድር ነው፡፡ ይህንን ሕግ አልቀበልም፤ እኮንነዋለሁም፡፡ ይህንን ሕግ የሰሩት ወንዶች ናቸው፤ ሕጉ ሴቶች ላይ የሚበረታውም ስለዚህ ነው፡፡››
የሚከተለውን ምንጭ ይመልከቱ፡- Patrologiae Graecae Tomus XXXVI: St. Gregorius Nazianzenus. ΛΟΓΟΣ ΛΖ’ (Migne, 1858).
በሌላ በኩል ደግሞ በኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰቦች ውሰጥ ከዘመኑ ታሪክ ጋር ተያይዘው ያሉት ማኅበረሰባዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ
እና ፖለቲካዊ ኩነቶች፤ በወቅቱ ነገረ-መለኮታዊ ትምህርቶች በካህናት እና አገልጋዮች የሚታዩበትን መንገድ እና በካህናቱ በኩል
ለምዕመኑ የሚደርሱበት ዘዴ ላይ ተጽእኖን ማሳደራቸው አይቀርም11፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
በገነነችባቸው አካባቢዎች ላይ የሚካሄዱ ውይይቶች እና ስብከቶች ከፖለቲካዊ፣ ማኅበረሰባዊ፣ ባህላዊ እና ሌሎችም የተለያዩ
አቅጣጫዎች አንጻር እንዲቃኙ በመሆናቸው ለመበረዝ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች፤ የኦርቶዶክስ
አባቶች ምንም እንኳ በተለያየ ዘመን ቢኖሩም፤ ያንጸባርቁት ከነበረው እና ታሪካዊ መሠረት ካለው ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ
(ፍሮኒማ) ተለየቶ ሊታይ ይገባዋል፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ኦርቶዶክሳዊ ሥራዎች


ኦርቶዶክስ ማለት በበዓለ አምሳ ለሐዋርያት የተገለጠው ቀጥተኛ (ኦርቶ) የሆነ እምነት (ዶክሳ) ነው፡፡ ከዚህ እምነት ውስጥ
የተወሰነው በቅዱሳት መጻሕፍት የሰፈረ ሲሆን፤ በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት መሠረት ግን በቅዱሳት መጻሕፍት ከሰፈረው ባልተናነሰ
መልኩ ቤተክርስቲያን በዘመናት ውስጥ ባለፈችበት ሂደት እና በቅዱሳኑ ሕይወት በኩል የተገለጸው ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትም
እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ቅዱሳን መጻሕፍት የክርስቲያናዊ ትውፊትን አስፈላጊነት የሚገልጹ ሲሆን ክርስቲያናዊ ትውፊት ደግሞ
የቅዱሳን መጻሕፍትን ትምህርት እና አስፈላጊነት ያጸናል፡፡ ይህ ቅዱስ ትውፊት ሳይበረዝ በቤተክርስቲያን በኩል ከክርስቶስ
እንደተቀበልነው ሆኖ የሚገኝ ነው፡፡ ይህም ትውፊት የኦርቶዶክሳውያን አባቶች አስተምህሮን፣ የቤተክርስቲያን ጉባኤያት
ውሳኔዎችን12 እና በአጠቃላይ የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወትን የቀረጹ ነገሮችን የሚያጠቃልል ነው፡፡

የዚህ ኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ማዕከል ላይም የምናገኘው በአዳምና ሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት የተከሰተውን ውድቀት ተከትሎ
የመጣውን የባሕርይ መጎስቆል ለማዳን የሚያስችለውን የነገረ-ድኅነት ትምህርት ነው፡፡ በዚህ ትውፊት መሠረት የመጀመሪያዎቹ
ሰዎች አዳም እና ሔዋን በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል የተፈጠሩ ቢሆንም ባለመታዘዛቸው ምክንያት ይህንን አምሳል
መጠበቅ አልቻሉም፡፡ ኦርቶዶክሳውያንም ከእግዚብሔር ጋር ኅብረት በመፍጠር እንዲለብሱ የተጠሩትም ይህንኑ አምሳል ነው፡
፡ በዚህ ትግል ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን የውድቀት መዘዝ የሆነውን ወደ ኃጢአት የሚያዘነብል ማንነታቸውን (ሥጋዊ ፍላጎቶች፣
ዘረመላዊ ዝንባሌዎች፣ መልካም ያልሆኑ ጠባዮች…ወዘተ) መጋፈጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ትግል ከባድ የሚያደርገው ደግሞ
በእግዚአብሔር ላይ ያመጸው እና የሰው ልጅ ዘለዓለማዊ ጠላት በሆነው ሰይጣን እና ጭፍሮቹ የሚኖረው ፈተና ነው፡፡

የኦርቶዶክስ አማኞች ወደ ኃጢያት የሚያዘነብለውን ባሕርይ በጸሎት፣ ምናኔ እና ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ (ፍሮኒማ) በማጎልበት
እንዲዋጉት የተጠሩ ናቸው፡፡ የዚህ ውጊያ የመጨረሻ ግቡም ከእግዚአብሔር ጋር ከሚኖር ኅብረት የሚመነጭ ጭምትነትን እና
ፍቅርን ገንዘብ ማድረግ ነው፡፡ ሊቁ ማክሲሞስ እንደሚገልጸውም የፈውሱ መንገድ ንጹሕ መሆን (Purification)፣ ከመንፈስ
ቅዱስ የሆነ አብርሆት (Enlightenment) እና እግዚአብሔርን መምሰል (Theosis)13 ነው፡፡ ምዕመኑ በመንጻት ሂደት ውስጥ
ሲያልፍ አብርሆትን ማግኘት እና ምሥጢራትን ከእግዚአብሔር በተገለጠለት ልክ መረዳት ይጀምራል፡፡ ይህም ልቦናን14
የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ጥበብ ለመቀበል የተነቃቃ ያደርገዋል፡፡ ይህንንም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመገለጥ ነገረ-መለኮት

11
ለአብነት ያህል፡- ታሪካዊ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ምዕመናንን በተመለከተ ኤልሳቤጥ ጋዚን ስትጽፍ እንዲህ ትላለች - ‹‹እነዚህ ማኅበረሰቦች ኦርቶዶክስ
ይባሉ እንጂ፣ የአካባቢው ዘመናዊ ታሪክ ቃኝተን ቤተክርስቲያን ልጆቿን በተገቢው መንገድ እንድታስተምር የማይፈቅዱ ኢስላማዊ እና ኮሚኒስት
ኃይሎች እንደነበሩባት ስንረዳ፤ ከዚህ አንጻር እውነተኛው ኦርቶዶክሳዊ ኤቶስ-ባሕርይ ምን ያህል በእነዚህ ማኅበረሰቦች ውስጥ ሊገኝ እንደሚችል ጥያቄ
ማንሳታችን አይቀርም፡፡›› የሚከተለውን ምንጭ ይመልከቱ፡- Elizabeth Gassin, “Eastern Orthodox Christianity and Men’s Violence
against Women” in Religion and Men’s Violence against Women, A. Johnson, ed. (Springer: New York, 2015), 165.
12
ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የቅዱሳን አባቶች ትውፊት እና የቤተክርስቲያኒቷ ሲኖዶሳዊ የጉባኤ ውሳኔዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የጉባኤ ውሳኔዎች ተቀባይነት
ያላቸው በተሳተፉባቸው አባቶች ምክንያት ነው፡፡ እነዚህ አባቶች በእምነታቸው በመጽናት እና ሃዋርያዊ አስተምህሮን በመጠበቅ ቅድስናቸውን
አስመስክረዋል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተግሳጾችም ቢሆኑ ተቀባይ ሊሆኑ የቻሉት እርሱ አንደበ-ርቱዕ ተናጋሪ ስለነበረ ሳይሆን በእርሱ ውስጥ ባደረው
የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አማካኝነት የሃዋርያት ትምህርትን ጠብቆ በማስተማሩ ነው፡፡
13
«θέωσις»; የሚለው ሲተረጎም ‹አምላካዊ ማድረግ› ወይም ‹እግዚአብሔርን መምሰል› ማለት ነው፡፡
14
«νοῦς»; ማለት የሰው ልጅ ነፍስ ማዕከል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፤ በዚህም ከአእምሮ ይለያል፡፡ ‹የነፍስ ዓይን› ተብሎም ይጠራል፡፡
[noetic theology] ትለዋልች፡፡ በሌላ አገላለጽ፤ ነገረ-መለኮታዊ መገለጡ የቆመው በአመክንዮአዊ አረዳድ እና አእምሯዊ
ጥበብ ሳይሆን በልቦና ንቃት እና ማስተዋል ላይ ነው፡፡

የዚህ የመገለጥ ነገረ-ድኅነት እና ነገረ-መለኮታዊ አስተምህሮ እንደሚያመለክተው ከሆነ ሴቶች ከዚህ ቅዱስ ትውፊት ውስጥ
ቦታ ለመነፈጋቸው በቂ ምክንያት እንደሌለ ነው፡፡ እንዲያውም ሐዋርያዊ ትውፊትን በመጠበቅ እና በመያዝ ደረጃ የሴቶች
ድርሻ ከፍተኛ ነበር፡፡ የዚህ ጽሑፍ አንባቢዎችም በታሪክ ውስጥ ብዙውን ነገረ-መለኮታዊ ገለጻዎች ያደረጉት ወንዶች
መሆናቸውን ተመሥርተው ነገረ-መለኮት በጾታዊ ማንነት ላይ መሠረቱን የጣለ እንደሆነ ማሰብ የለባቸውም፤ ይህ የሆነበት
ቤተክርስቲያናዊ፣ ማኅበረሰባዊ እና ባህላዊ ምክንያት አለውና፡፡15 የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታሪክ ውስጥ ሴቶችም ሆነ
ወንዶች ቅዱሳንን እና ነቢያትን እንደምትዘክር፣ አልፎም ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹ቅድስተ ቅዱሳን› መሆኗ እንደምታምን
የታወቀ ነው፡፡ በተጨማሪም ቅዱሳን ሴቶች ነገረ-መለኮታዊ አስተምህሮን ፍጹም በሆነ ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ ለቅዱሳን አባቶች
ሰማያዊ ምሥጢራትን ያስረዱበት ሁኔታ እንደነበረ16 እና በካህናት መካክል የነበሩ ዶግማዊ [አስተምህሯዊ] ጉዳዮችን የወሰኑበት
ሁኔታ እንደነበር ከታሪክ እንረዳለን፡፡17

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች ሲነበቡ በትርጓሜዎቹ ደጋግሞ ባስተጋባው እና ባስረገጠው ኦርቶዶክሳዊ በሆነው የዓለም
አተያይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሐዋርያት ትምህርት ላይ ተመሥርቶ የወንዶች እና ሴቶችን መንፈሳዊ
እኩልነት አስተምሯል፤ በዚህም ሴቶች ለቤታቸው፣ ለባላቸው እና ለቤተሰቦቻቸው መንፈሳዊ ተሐድሶን እንዲፈጥሩ የሚያደርግ
አቅምን አጎናጽፏቸዋል18፡፡ ሆኖም ግን ትምህርቶቹ በሚነበቡበት ጊዜ ከተገቢው ታሪካዊ ዐውድ አንጻር እና በወቅቱ ከነበረው
ከምዕመናን እና በተለይ ከሴቶች ነባራዊ ሁኔታ ተነጥሎ መታየት የለበትም፡፡19 ከአባታዊ ርሕራሄው በመነጨ መልኩ በወቅቱ
የሚያስተላልፈው መልእክት ለሰሚው የተመቸ እና አሳማኝ እንዲሆን ወቅቱን ማዕከል ያደረገ ቋንቋ፣ አገላለጽ እና የንግግር
ዘይቤ መጠቀሙንም ማወቅ ይኖርብናል፡፡20

በኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ (ፍሮኒማ) ሁኔታዎችን መቃኘት ማለት ሊቃውንት ፍጹም የማይስቱ [Infallible] አለመሆናቸውን -
በአስተምህሮዎቻቸው መካከል እርስ በእርስ መስማማት መኖር እንዳለበት እና አልፎም ደግሞ አስተምህሮዎቻቸው ከሐዋርያትን

15
የዚህ ዋነኛ ምክንያት በቀደምት ማኅበረሰቦች ውስጥ ወንዶች ከፍ ያለ እርከንን ይዘው እንደነበር እና ሴቶች ደግሞ በአጠቃላይ የቤት ሥራዎች እና
ልጅ ማሳደግ ላይ ያተኩሩ እንደነበር በማጤን የሚፈታ ነው፡፡ በተጨማሪም በኦርቶዶክስ አስተምህሮ መሠረት የክህነት ቦታን ሸፍኖ የሚያገለግለው
ወንድ በመሆኑ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አይነት ብዙ የሚጽፉ አባቶች እንዲወጡ ምክንያት ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የክህነት
ቦታን ለወንዶች የምትሰጠው የወንድ ልጅ የበላይነትን ስለምትቀበል ሳይሆን ራሱን በቻለ ነገረ-መለኮታዊ ምክንያት ነው፡፡ ይህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
በአንዳንድ ኦርቶዶክስ ሊቃውንት ዘንድ መወያያ ርዕስ ሆኗል፡፡
16
ይህ በግልጽ የሚታየው ቅድስት ማክሪና ከወንድሟ ከቅዱስ ጎርጎሪዎስ ዘኑሲስ ጋር ነፍስን በተመለከተ ያደረገችው ውይይት ነው፡፡ ይህ ወይይት ቅዱስ
ጎርጎሪዎስ እንደቀደሞው ሁሉ በእምነቱ ጠንክሮ እንዲጓዝ ረድቶታል፡፡ ቅድስት ማክሪናንም መምህሩ እንደሆነች ያስብ ነበር፡፡
17
ይህ በአራተኛው የኬልቄዶን ጉባኤ (451 ዓ.ም) ላይ የታየ ሲሆን፤ በነገረ-ክርስቶስ ዙሪያ የተወሰነው የመጨረሻ ውሳኔ የተወሰነው በቅድስት ኢውቴሚያ
ተዓምር ነበር፡፡
18
የሚከተለውን ምንጭ ይመልከቱ፡- David C. Ford, Women and Men in the Early Church: The Full Views of St. Chrysostom
(South Canaan, Pennsylvania: St. Tikhon’s Seminary Press, 1996).
19
የሚከተለውን ምንጭ ይመልከቱ፡- Deborah F. Sawyer, Women and Religion in the First Christian Centuries (New York:
Routledge, 1996).
20
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሴቶች ከወንዶች አንጻር ደካማ ስለመሆናቸው እና ለእርዳታ ዝቅ ማለት እንደሚኖርብን ማስተማሩ የሚካድ አይደለም፡፡ (In
Epistulam ad Ephesios, Homily 20). በተለያዩ ቦታዎችም ሴቶች የበለጠ ወሬኛ እና ብስለት የጎደለው መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ (De
Virginitate, Paragraph 40). እነዚህ ቃላቶች በቀደምት ጊዜ ከነበረው የሴቶች ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ሊቃኝ ይገባዋል፡፡ ከክርስትና በፊት በነበሩ
ጊዜያት ሴቶች ከወንዶች ያነሱ ተደርገው ይታዩ ስለነበር፤ ሃሳባቸውን ሊሞርዱበት የሚችል ትምህርት የሚያገኙበት እድል እጅግ ዝቅተኛ ነበር፤ ይሄም
ደግሞ ብስለት የጎደለው ስለመሆናቸው የሚታሰበው እንዲጸና የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ሆኖም ግን ቅዱስ ዮሐንስ ይህንን ስለሴቶች ቢናገርም፤
ወንዶችም ቢሆኑ ተናዳጅ፣ ትዕቢተኛ እና ግፈኛ ስለመሆናቸው ተናግሯል፡፡ (De Virginitate, Paragraph 40). በዚህ መንገድ በመናገርም ወንዶችም
ሆነ ሴቶች በትዳር ውስጥ የአንዳቸውን ችግር ተረድተው የትዳር ነገረ-ድኅነታዊ ዓላማ የሆነውን ሕብረት እንዲያሳኩ የሚረዳቸውን ክርስቲያናዊ አካሄድ
እንዲያዳብሩ ለማድረግ ሞክሯል፡፡ የሚከተለውን ምንጭ ይመልከቱ፡- «Ο Άγιος Ιωάννης ο Χρυσόστομος και η Οικογενειακή Ζωή του
Αρχιμ. Εφραίμ, Καθηγούμενου Ιεράς Μεγίστης Μονής Βατοπαιδίου. Πηγή: Περιοδικό ‘Πεμπτουσία’ Νο 25»,
republished by OODE, April 18, 2008, http://www.oodegr.com/oode/koinwnia/oikogeneia/xrysost_oikog_zwi1.htm).
ትምህርት ጋር የማይጣረሱ መሆን እንዳለባቸው መገንዘብ ነው፡፡ በሌሎች ዶግማዊ ወይም ነገረ-መለኮታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች
ላይ ግን የቅዱሳን አባቶች አስተምህሮ በምክር ለጋሽነት ሊወሰድ የሚገባ ነው፡፡ እነዚህ ምክር ለጋሽ አስተምህሮዎች
በሕይወታቸው መቃኘት የኦርቶዶክሳዊ ምእመናን የግል ምርጫቸው21 ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ (ፍሮኒማ) መረዳት
ማለት ታዲያ ቀደም ብለን የተረዳናቸውን የኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ጠባዮች እና በትርጓሜ ዙሪያ ያሉ እይታዎችን መረዳት ማለት
ነው፡፡ በእርግጥ ትውፊቱ የቤተክርስቲያን አባቶችንም ሆነ ሐዋርያዊ ትውፊቱን ጠብቀው የጻፉ ዘመናዊ ሊቃውንትን ጽሑፎች
በማንበብ መረዳት ቢቻልም፤ ይህ ንባብ ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚኖር ተግባር ተኮር ሕይወት ካልተደገፈ በስተቀር
በጉዳዩ ዙሪያ ጥሩ የሆነ አረዳድ አይኖርም፡፡ የዚህ ጥናት ጸሐፊም የምታቀርበው እይታ በኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት (ኑሮ) ውስጥ
በማለፍ እና በማጥናት ያካበተችው መሆኑን ማጤን መልካም ይሆናል፡፡22

የጥናት ዘዴ
ይህ ጥናት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ዙሪያ የጻፋቸውን ስብከቶች በጥንቃቄ በማንበብ እና በመመርመር የተዘጋጀ ነው፡፡
የዚህ ጥናት ጸሐፊ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ሀያ የተለያዩ ስብከቶች በተጻፉበት ጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ ያነበበች ሲሆን ከእነርሱ
መካከል ሰባቱ በዚህ ጥናት ላይ ተጠቅሰዋል፡፡23 ትኩረት ሊሰጣቸው የተገቡት ስብከቶች የተመረጡትም፡ ሀ) የትዳር ግንኙነትን
በተመለከተ ከመጽሐፍ ቅዱስ (በተለይ ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት) የተውጣጡ ጥቅሶች እና ለ) በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሥራ ላይ በእንግሊዝኛ ወይም በግሪክ ቋንቋ የተጻፉ ምንጮች በመሆናቸው ነው፡፡ ይህ ጥናት እጅግ ጥልቅ ሊባል ባይችልም
እንኳ በተመረጡት ርዕሶች ዙሪያ ጠቅለል ያለ ኦርቶዶክሳዊ አረዳድን ለመፍጠር ሙከራ የተደረገበት ነው፡፡

በዚህ ሥራ ላይ የተጠቀሱት የጥንታዊ ግሪክ ምንጮች በቀጥታ በህዳግ ማስታወሻ እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡ የዚህም ምክንያት
መዛግብቱ የተጻፉበት ጥንታዊ ቋንቋ መሠረት በማድረግ ተገቢ የሆነ የትርጓሜ ዐውድ ለማስቀመጥ ስለሚረዳ ነው፡፡ ለዚህ
ሥራ እንደ ግብዓትነት የዋሉትን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሥራዎች የተረጎሙት ምንጮች በአብዛኛው ሥራዎቹን
ለመተርጎማቸው ምክንያትም ሆነ የተጠቀሙበትን የትርጓሜ መንገድ ግልጽ አላደረጉም፡፡ ሆኖም ግን የግሪክ ቋንቋ ሰፊ የትርጓሜ
ዐውድ ከማካተቱ አንጻርና ቀደምት ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ቁልፍ ቃላቶችን በተገቢው ኦርቶዶክሳዊ ዐውድ በማድረግ ብያኔ
መስጠታቸውን ታሳቢ በማድረግ24 በትርጓሜ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል፡፡ ሆኖም ግን ካለን ውስን ቦታ አንጻር በዚህ ጥናታዊ
ጽሑፍ ላይ እንዲህ ማድረግ አልተቻለም፡፡ የእንግሊዝኛ ትርጉም ያላቸው ሥራዎችን አንባቢ በቀላሉ እንዲያገኛቸው
በምንጭነታቸው በቀጥታ ተጠቅሰዋል፡፡ የዚህ ጥናት ጸሐፊ ያስተካከላቸውን እና በህዳግ ማስታወሻ የተጠቀሱት ሥራዎች ግን
ጸሐፊውን በመጠየቅ ማግኘት ይቻላል፡፡25

በአብዛኞቹ የትርጉም ሥራዎች ላይ ‹ትዳር› ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል ‘γάμος’ [ጋሞስ] የሚለው ነው፡፡ ሆኖም ግን
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ቃል በተጠቀመባቸው ቦታዎች ሁሉ ‹ትዳር› ብሎ መተርጎም (በተለይ ከሰው ልጅ ውድቀት
በኋላ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ስንናገር) የቃሉን ሰፊ አንድምታ ያኮስሰዋል ምክንያቱም ከጾታዊ ግንኙነት ነጻ ስለሆነው እና
በሰማይ ስላለው ኅብረት ሲጽፍ ‘γάμος’ የሚለውን ቃል ጾታዊ መሳሳብ የሌለበትን ግንኙነትም ለመጥቀስ ይጠቀምበታልና

21
‘διάκρισις’; የሚለው ቃል ትርጓሜ ‹መለየት መቻል› የሚል ነው፡፡ ይህም በጸሎት እና በምናኔ ሕይወት የሚመጣ ነው፡፡
22
የዚህ ጥናት ጸሐፊ የተወለደችው በሞልዶቫ ሪፐብሊክ ሲሆን ያደገችውና የተማረችው ደግሞ በግሪክ ነው፡፡ ሁለቱም ሀገሮች ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናንን
በሰፊው የያዙ ናቸው፡፡
23
እነዚህ ሥራዎች የተገኙት ከኤጊያን ዩኒቨርሲቲ Migne’s Patrologia Graeca ምህዳር ነው፡፡
24
የሚከተለውን ምንጭ ይመልከቱ፡- Panayiotis Nellas, Deification in Christ: Orthodox Perspective on the Nature of the Human
Person (New York: St Vladimir’s Press, 1987), 16.
25
በዚህ ያሉት አንዳንድ የእንግሊዝኛ አንድምታዎች ከእንግሊዝኛ ጸሐፊያን ሥራዎች ላይ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ጥናት ጸሐፊ እንደ
አስፈላጊነቱ የኦሪጅናሉን ግሪክ ምንጭ በመመልከት ጥቃቅን እና ትላልቅ ለውጦችን አድርጋለች፡፡ እነዚህን ለውጦች ለማየት እንዲያመች ጠመም ባለ
ፊደል እንዲሰፍሩ ተደርገዋል፡፡
ነው፡፡26 የሰው ልጅ ከገነት ከተባረረ በኋላ ግን ጾታዊ ግንኙነት በትዳር ማዕቀፍ ውስጥ ገብቶ የሰው ልጅን የድኅነት ጎዳና
የሚያሳልጥ ምሥጢራዊ እና መንፈሳዊ ግንኙነት አካል ሆኗል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ከሆነ እግዚአብሔር
የአዳምን ውድቀት ስለሚያውቅ አስቀድሞ በወንድ እና በሴት መካከል ከፍተኛ የሆነ መቀራረብን ፈጥሯል፡፡ ይህም ደግሞ
ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ በትዳር በኩል ለሚገኘው የሰው ልጅ ድኅነት አስተዋጽኦን የሚያደርግ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ስለ ትዳር በሚያወራበትም ጊዜ የሚያወራው ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ ስላለው የትዳር ጥምረት ሲሆን፤ ይህም ደግሞ በሰማይ
ካለው ጥምረትም ሆነ ከድንግልና ሕይወት የተለየ ነው፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮዎች ዳሰሳ


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ዙሪያ የሚያስተምረውን ትምህርት ጠንቅቆ ለማወቅ አስቀድመን የአዳም እና ሔዋንን አፈጣጠር
እና ባለመታዘዛቸው ምክንያት ያጋጠማቸውን ስደት ማጤን ይኖርብናል፡፡

በኦሪት ዘፍጥረት ላይ የሰጠውን ትርጓሜ ስንቃኘው ሴቷ ከወንዱ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ እና በተመሳሳይ ክብር ሆና መፈጠሯን
አጽንኦት ይሰጠዋል፡፡27 ወንድ እና ሴት አስቀድመው አንድ የመሆናቸውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትም በተደጋጋሚ ያነሣል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ኤፌሶን ሰዎችን በተረጎመበት ድርሳኑ ላይም ይህንን ትምህርት ካጸና በኋላ28 አዳም እንደርሱ
ያለች ረዳት እንደተፈጠረችለት ሲያውቅ ‹‹አጥንቷ ከአጥንቴ›› እና ‹‹ሥጋዋ ከሥጋዬ›› ማለቱን ይነግረናል29፡፡ በተጨማሪም የሴት
ልጅ ከወንድ መፈጠር ራሱን የቻለ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን እና ይህም ደግሞ አዳም በምንም ሁኔታ ከእርሱ የተለየች
ፍጡር እንደሆነች አድርጎ እንዳያያት እንደሆነ ይገልጽልናል30፡፡

በጉዳዩ ላይ ያለውን ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ በሚያጸና መልኩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ከሆነ የእግዚአብሔርን
ትእዛዝ ከመጣሳቸው በፊት በሁለቱ መካከል የሥጋ ውሕደት እንዲፈጠር የሚያደርግ ጾታዊ መሳሳብ አልነበረም፤ አዳምና
ሔዋንም እርስ በእርስ በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ላይ ያጠነጠነ ግንኙነት ውስጥ ነበሩ፡፡ በድንግልና ሕይወት ዙሪያ በጻፈው
ድርሳን ላይ አዳምና ሔዋን በገነት እያሉ እንደ ሕጻናት ንጹሓን ነበሩ፤ ከእግዚአብሔር ጋርም ቀጥተኛ ግንኙነት ስለነበራቸው
በሕይወታቸው ደስተኛ ነበሩ ይላል31፡፡ ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ምክንያት ግን በኃጢአት አደፉ፤ ይሄም የእርስ በእርስ
ግንኙነታቸውን ቀየረው፡፡ የሴት ልጅም እግዚአብሔር ከአዳም ከወሰደው አጥንት በሠራት ጊዜ በተፈጥሮ ላይ የተሰጣትን እኩል
መብት ያጣችው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ከሆነም ላለመታዘዛቸው ባደረገችው አስተዋጽኦ
ምክንያት በባሏ ላይ ጥገኛ እንድትሆን ተደርጋለች32፡፡ ሆኖም ግን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህ የተደረገው እንደ ቅጣት ሳይሆን

26
ይህንን ግልጽ ለማድረግ «γάμος» የሚለውን ቃል ምንጭ ማየት ነው፡፡ የቃሉ ምንጭ ትርጉም ‹አብሮ መተኛት› («γαμέω/γαμώ») የሚል ነው።
27
«πόσης εὐφροσύνης αὐτοῦ ἡ ψυχὴ ἐνεπίμπλατο κοινωνὸν θεωρῶν τὴν γυναῖκα, καὶ ὁμότροπον καὶ ὁμόδοξον
αὐτὴν καθεστῶσαν;» In Genesim (sermo 3).
28
«ὥσπερ καὶ ἡ Εὔα σὰρξ ἀπὸ τῆς σαρκὸς τοῦ Ἀδάµ.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
29
« Ἄκουε· Τοῦτο νῦν ὀστοῦν ἐκ τῶν ὀστῶν μου, φησὶ, καὶ σὰρξ ἐκ τῆς σαρκός μου». In Epistulam ad Ephesios, Homily
20.
30
አትኩሮቱን የሚያደርገው ሥጋ («σαρκὸς») እና አጥንት («ὀστῶν») ላይ ነው፡፡ ይህንንም ያደረገው በሁሉም ረገድ ሴቷ ከወንዱ ጋር በአንድ
አይነት ሁኔታ መፈጠሯን ለማጠየቅ ነው፡፡
31
«Πλασθεὶς δὲ ἐκεῖνος ἔμεινεν ἐν παραδείσῳ καὶ γάμου λόγος οὐδεὶς ἦν.Ἐδέησεν αὐτῷ γενέσθαι καὶ βοηθόν, καὶ
ἐγένετο, καὶ οὐδὲ οὕτως ὁ γάμος ἀναγκαῖος εἶναι ἐδόκει.Ἀλλ' οὐδὲ ἐφαίνετό που, ἀλλ' ἔμενον ἐκεῖνοι τούτου χωρὶς
καθάπερ ἐν οὐρανῷ τῷ παραδείσῳ διαιτώμενοι καὶ ἐντρυφῶντες τῇ πρὸς Θεὸν ὁμιλίᾳ.Μίξεως δὲ ἐπιθυμία καὶ
σύλληψις καὶ ὠδῖνες καὶ τόκοι καὶ πᾶν εἶδος φθορᾶς ἐξώριστο τῆς ἐκείνων ψυχῆς.» In De virginitate, Paragraph
14.Translation in Miller, Women, 109.
32
«Ἐποίησά σε, φησὶν, ὁμότιμον· οὐκ ἐχρήσω καλῶς τῇ ἀρχῇ· μετάβηθι πρὸς τὴν ὑποταγήν.Οὐκ ἤνεγκας τὴν
ἐλευθερίαν, κατάδεξαι τὴν δουλείαν.Οὐκ οἶδας ἄρχειν, καὶ δι' αὐτῆς τῶν πραγμάτων ἔδειξας τῆς πείρας· γενοῦ τῶν
ἀρχομένων, καὶ τὸν ἄνδρα ἐπίγνωθι κύριον.Πρὸς τὸν ἄνδρα σου ἡ ἀποστροφή σου, καὶ αὐτός σου κυριεύσει.» In
Genesim Sermones, Homily 4.Translation in Miller, Women
እንደ ስጦታ መሆኑን በመጥቀስ፤ ከውድቀታቸው በኋላ ሴቷ በብዙ ፍርሃት እና ችግር ውስጥ እንደምትገባ እግዚአብሔር
በማወቁ እንደሆነ ያብራራልናል፡፡ ይህንን በተመለከተም እንዲህ ይለናል፡-

እዚህ ጋር የእግዚአብሔርን ምሕረት ተመልከቱ፡፡ “እርሱም ገዢሽ ይሆናል” የሚለውን ቃል በሰማች ጊዜ ትልቅ ሸክም
እንደተጫነባት ማሰቧ አይቀርምና፤ ለዚህ ሲባል እግዚአብሔር የርሕራሄ ቃልን አስቀደመ፡፡ ይህንንም ያደረገው ‹‹ፈቃድሽም
ወደ ባልሽ ይሆናል›› በማለት ነው፡፡ ይህም ደግሞ ማለት ‹‹እርሱ ከለላሽ እና መከታሽ ነው፤ በየቀኑ በምትኖሪው ሕይወትሽ
ውስጥ እርሱ መከታ እና ከለላ ይሆንሻል፤ እኔም ወደ እርሱ ትሄጂ ዘንድ መብትን ሰጥቼሻለሁ›› ሲላት ነው፡፡ ይህንን መፍቀድ
ብቻ ሳይሆን በጾታዊ ስሜትም ሁለቱን አስተሳስሯቸዋል፡፡ ኃጢያት ሴቲቱ ፈቃዷ ወደ ባሏ እንዲሆን እንዳደረገ፤ ሆኖም
ግን አምላክ በቸርነቱ ይህንን ለእኛ መልካም ነገርን ለማድረግ እንዴት አድርጎ እንደተጠቀመበት ተመለከታችሁን?33

የሴቷ ከሥልጣን እርከን መውረድ ከገነት ስትወጣ ሊያስከትልባት ከሚችለው ፍርሃት እና ጉዳት ለመጠበቅ ሲል አምላክ
በአዳም እና በሔዋን መካከል ጾታዊ መሳሳብን አደረገ፡፡ በዚህም ሥርዓት ምክንያት ባል የሚስት ራስ የተደረገው ለእርሷ ከለላ
እንዲሆናት ሲሆን እርሷ፣ እግዚአብሔር ደግሞ በተፈጥሮ ሴቷ ወደ ወንዱ እንድትሳብ፣ እርሱም በተፈጥሮ እርሷን እንዲፈልጋት
አድርጓል፡፡ የዚህም ምክንያት ግንኙነታቸው የፍቅር እና የመተማመን እንጂ ፍራቻ የነገሠበት እንዳይሆን በሚል ነው፡፡ ይህ
የሆነው ደግሞ የሰው ልጅ ወደ ኃጢያት ለማዘንበል ካለው ፍላጎት እና ከውድቀት በኋላም ሰይጣን የሰውን ልጅ ድኅነት
ለማደናቀፍ ከሚያደርገው ከፍተኛ ሙከራ አንጻር ነው፡፡

እዚህ ጋር የሔዋን ከአዳም በታች የመሆን ጉዳይ እርሷ ሰፊ የሆነ ድርሻን ከተጫወተችበት ከመጀመሪያው በደል ጋር የሚገናኝ
ሲሆን እርሱ ግን እርሷን ብቻ የሚያስጠይቅ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ እንዲያውም፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አዳምን እኩል
ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፤ ስለአዳም በደል ምክንያት ባይሆን ኖሮ የሰው ልጅ ድኅነት ፈላጊ ባልሆነም ነበር34፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ
‹‹የመጀመሪያው ሰው በደል››35 በማለት ሲጽፍ እናነባለን፡፡ ይህ አካሄዱ በኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ የተቃኘ መሆኑን
የምናውቀውም፤ ጣት ከመጠቆም ይልቅ የተሰራው በደል የሚካስበት መንገድ ላይ ያተኮረ መሆኑን ስንገነዘብ ነው፡፡

በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት መሠረት፤ ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ ድኅነትን ለማግኘት ሁለት አማራጮች አሉ፡- የመጀመሪያው
በድንግልና የምናኔ ሕይወት መኖር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በጋብቻ ነው፡፡ ሁለቱም መንገዶች በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው ሲሆኑ በተለያዩ ዘመናት እነዚህን መንገዶች ለማጣጣል ከተነሱ መናፍቃን ቤተክርስቲያን
ጠብቃናለች፡፡ ሆኖም ግን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የድንግልና ምናኔ ሕይወት ከጋብቻ ሕይወት እንደሚበልጥ ያምን ነበር፤

33
«Καὶ ὅρα Θεοῦ ἐνταῦθα φιλανθρωπίαν. Ἵνα γὰρ μὴ ἀκούσασατὸ, Αὐτός σου κυριεύσει, φορτικὴν εἶναι νομίσῃ τὴν
δεσποτείαν, πρότεροντὸ τῆς κηδεμονίας ἔθηκεν ὄνομα εἰπὼν, Πρὸς τὸν ἄνδρα σου ἡ ἀποστροφή σου, τουτέστιν, Ἡ
καταφυγή σου καὶ ὁ λιμὴν καὶ ἡ ἀσφάλεια ἐκεῖνος ἔσται σοι· ἐν πᾶσι τοῖς ἐπιοῦσι δεινοῖς πρὸς ἐκεῖνον
ἀποστρέφεσθαι καὶ καταφεύγειν σοι δίδωμι. Οὐ ταύτῃ δὲμόνον, ἀλλὰ καὶ φυσικαῖς αὐτοὺς συνέδησεν ἀνάγκαις
καθάπερ ἄῤῥηκτόν τινα δεσμὸν, τὴν ἐκ τῆς ἐπιθυμίας περιβαλὼν αὐτοῖς ἅλυσιν. Εἶδες πῶς εἰσήγαγε μὲν τὴν
ὑποταγὴν ἡ ἁμαρτία, ὁ δὲ εὐμήχανος καὶ σοφὸς Θεὸς καὶ τούτοις πρὸς τὸ συμφέρον ἡμῖν ἀπεχρήσατο;» In Genesim
Sermones, Homily 4. Original translation in Miller, Women, 30 with underlined alterations.
34
«Ὥσπερ οὖν τότε ἀπὸ νεκρῶν σωμάτων τοσαύταις μυριάσι δέδωκεν ὑπόθεσιν καὶ ῥίζαν ὁ Θεός, οὕτω καὶ παρὰ τὴν
ἀρχὴν εἰτοῖ ςπροστάγμασιν αὐτοῦ πεισθέντες οἱ περὶ τὸν Ἀδὰμ τῆς ἡδονῆς ἐκράτησαν τοῦ ξύλου, οὐ κἂν ἠπόρησεν
ὁδοῦδι'ἧς τὸ τῶν ἀνθρώπων γένος αὐξήσει.» De Virginitate, Paragraph 15. Translation in Miller, Women, 110.
35
ለአብነት ያህል፡ Genesim (sermo 3) ላይ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች “τὸν πρῶτον ἄνθρωπον” ጾምን መጠበቅ ስላቃታቸው ገነትን ማጣታቸውን
ይነገረናል፡፡ ‘ἄνθρωπος’ (በግሪክ ቋንቋ ‹ሰው›ማለት ነው) የሚለው ቃል ምንጭ አከራካሪ ቢሆንም፣ ብዙዉን ጊዜ ግን ‘ἄνδρ-ωπος’ ከሚለው
ቃል ጋር የሚገናኝ ነው፤ እርሱም ደግሞ የሰው (ἀνήρ). መልክ ያለውን አንድ አካል የሚጠቁም ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹ሰው› እና ‹ወንድ›
የሚሉትን ቃላት በመለያየት ስለሚጠቀማቸው፤ እዚህ ጋር አዳምን ብቻ ማለቱን እንደሆነ ያጠራጥራል፡፡ ይህ ቢሆንም ሔዋንን ብቻ ጥፋተኛ አድርጎ
አለመናገሩን የሚደግፍልን መከራከሪያ ነጥብ ነው፡፡
ለዚህም ደግሞ ምክንያቶች ነበሩት፡፡ ይህም በወንድ እና በሴት መካከል ያለው ጾታዊ መሳሳብ የሰው ልጅ ውድቀት ውጤት36
መሆኑን እና አስፈላጊም የሆነውም በሰው ልጅ ድካም37 ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡ የድንግልና ሕይይወት ግን ከሰው
ልጅ ውድቀት በፊትም በመላእክት ዘንድ ሳይቀር ነበር38፡፡ በመሆኑም፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ከሆነ፣ አንድ
ሰው ወደ ሰማያዊ ሕይወት የበለጠ ለመቅረብ ከፈለገ የድንግልና ሕይወትን ይኖራል፡፡

በተጨማሪም በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜዎች ላይ የድንግልና ሕይወት በትዳር ሕይወት ውስጥ ከሚገኙ ዓለማዊ ሃሳቦች
የነጻ መሆኑ ተጽፏል፡፡ በምናኔ ሕይወት ውስጥ አንድ ሰው ሙሉ ለሙሉ ራሱን ለመንፈሳዊ ተግባራት በመስጠት እና ለነፍስ
ድኅነት በመታገል መኖር የሚችል ሲሆን፤ በጋብቻ ሕይወት ውስጥ ግን ባለትዳሮች በዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ መግባት እና
ለራሳቸውም ሆነ ለቤተሰብ አባላቶቻቸው ዓለማዊ እና መንፈሳዊ ሕይወት መጨነቅ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም፣ አንድ ትዳር
መንፈሳዊ እንዲሆን ከተፈለገ በጋብቻ ውስጥ ያሉት አካላት እንዳልተጋቡ ሆነው መኖር አለባቸው - ይህም የቅዱስ ጳውሎስን
‹‹ሚስቶች ያሏቸው እንደ ሌላቸው ይሁኑ››39 የሚለውን ቃል የሚያስተጋባ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ይህንን
ተንተርሶ እንዲህ ብሎ ይጠይቃል፡- ‹‹ከወሰድነው በኋላ እንዳልወሰድነው የምንሆን ከሆነ መውሰድ ስለምን ያስፈልጋል;››40

በተጨማሪም ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚነግረን ከሆነ ጋብቻን መረዳት ያለብን ወንዶች እና ሴቶች ኃጢያትን አሸንፈው ቅድስናን
ገንዘብ ሊያደርጉ እንደሚችሉበት ምሥጢር ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከውድቀት በኋላ በሰው ዘንድ ከፍተኛ ፈተና
የሆኑትን እና ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረገውን ኅብረትም ከሚከለክሉ ኃጢያቶች፣ ማለትም ከዝሙት እና ገላን ከመቸርቸር
ራስን ለመጠበቅ ትዳር ጠቃሚ መሆኑን ትመክራለች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን የትዳር ዓላማ በሰዎች ዘንድ ዘውትር በዚህ መልኩ
ጥንቅቅ ተደርጎ እንደማይቀመጥ እና ብዙ ትኩረት የሚሰጠው የትዳር ዓላማም ልጅ መውለድ እንደሆነ ይገልጻል፡፡41
ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ ዘርን ማስቀጠል እና ለሰው ልጅ ድኅነት የተዘጋጀው እቅድም እንዲፈጸም ማድረግ ይገባ ነበር፡፡
ሆኖም ግን እግዚአብሔር ትዳርን የሰጠበት ዋነኛው ምክንያት የሰው ልጅ ኃጢያትን እንዳያሸንፍ እንቅፋት የሆኑትን ያልተገቡ
ፍላጎቶች ማስወገድ ነበር42፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ለማጠየቅ የሚያነሣው ብዙዉን ዘመናቸውን ያለ ልጅ የኖሩትን

36
«Ἀπὸ τῆς παρακοῆς, ἀπὸ τῆς ἀρᾶς, ἀπὸ τοῦ θανάτου. Ὅπου γὰρ θάνατος, ἐκεῖ γάμος.» De Virginitate, Paragraph
14.Translation in Miller, Women, 109.
37
Original being «ἀσθένειαν».
38
«Ἀλλ' οὐχ ἡ παρθενία ταύτην ἔχει τὴν ἀκολουθίαν ἀλλ' ἀεὶ χρήσιμον, ἀεὶ καλὸν καὶ μακάριον καὶ πρὸ τοῦ θανάτου
καὶ μετὰ τὸν θάνατον καὶ πρὸ τοῦ γάμου καὶ μετὰ τὸν γάμον». De Virginitate, Paragraph 14.
39
1 ቆሮንጦስ 7፡29
40
«τί χρὴ λαβεῖν τοσοῦτον ὄγκον, ὅταν καὶ μετὰ τὸ λαβεῖν οὕτω δέοι χρῆσθαι, ὡς μὴ ἔχοντα;» In Epistulam i ad
Corinthios, Homily 19.Original translation from Schaff, NPNF1-12, 194.
41
«Ὅτι πάλαι μὲν τῷ γάμῳ δύο προφάσεις, νῦν δὲ μία. Ἐδόθη μὲν οὖν καὶ παιδοποιΐας ἕνεκεν ὁ γάμος· πολλῷ δὲ
πλέον ὑπὲρ τοῦ σβέσαι τὴν τῆς φύσεως πύρωσιν. Καὶ μάρτυς ὁ Παῦλος λέγων· “∆ιὰ δὲ τὰς πορνείας ἕκαστος τὴν
ἑαυτοῦ γυναῖκα ἐχέτω”, οὐ διὰ τὰς παιδοποιΐας. Καὶ πάλιν ἐπὶ τὸ αὐτὸ συνέρχεσθαι κελεύει οὐχ ἵνα πατέρες
γένωνται παίδων πολλῶν, ἀλλὰ τί; “Ἵνα μὴ πειράζῃ ὑμᾶς ὁ σατανᾶς”, φησί. Καὶ προελθὼν δὲ οὐκ εἶπεν· εἰ δὲ
ἐπιθυμοῦσι παίδων, ἀλλὰ τί; “Εἰ δὲ μὴ ἐγκρατεύονται, γαμησάτωσαν.” Παρὰ μὲν γὰρ τὴν ἀρχήν, ὅπερ ἔφην, δύο
ταύτας εἶχε τὰς ὑποθέσεις· ὕστερον δὲ πληρωθείσης καὶ τῆς γῆς καὶ τῆς θαλάττης καὶ τῆς οἰκουμένης πάσης μία
λείπεται πρόφασις αὐτοῦ μόνη, ἡ τῆς ἀκολασίας καὶ ἡ τῆς ἀσελγείας ἀναίρεσις.» De Virginitate, Paragraph 19.
Translation in Miller, Women, 113.
42
Predicting that he could be blamed for denigrating the laws of Moses, Chrysostom reassuredly explained: «Κακίζω
μὲν οὐδαμῶς· Θεὸς γὰρ αὐτὰ συνεχώρησε καὶ γέγονεν ἐν καιρῷ χρήσιμα. Μικρὰ δὲ αὐτὰ εἶναί φημι, καὶ παίδων
κατορθώματα μᾶλλον ἢ ἀνδρῶν. Καὶ διὰ τοῦτο ἡμᾶς τελείους ὁ Χριστὸς δημιουργῆσαι βουλόμενος ἐκεῖνα μὲν
ἀποθέσθαι ἐκέλευσεν, ὥσπερ ἱμάτια παιδικὰ καὶ οὐ δυνάμενα περιβάλλειν τὸν ἄνδρα τὸν τέλειον οὐδὲ τὸ μέτρον
κοσμῆσαι τῆς ἡλικίας τοῦ πληρώματος τοῦ Χριστοῦ, τὰ δὲ ἐκείνων εὐπρεπέστερα καὶ τελειότερα περιθέσθαι
ἐκέλευσεν, οὐκ ἀντινομοθετῶν ἑαυτῷ ἀλλὰ καὶ σφόδρα ἀκολουθῶν.» De Virginitate, Paragraph 16. Translation in
Miller, Women, 110-111.
አብርሃም እና ሳራን ነው፡፡ የአብርሃም እና የሳራ ጋብቻ ለአብርሃም የሚፈልገውን ልጅ የሚያገኝበት መንገድ ሊሆን እንዳልቻለ43
በመጠቆም፤ ይህም ደግሞ ሰዎች ለመራባት ከፈለጉ ይህንን የሚያደርጉት በራሳቸው ጾታዊ ስሜት በኩል ወይንም በትዳር
ስለታቀፉ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት›› የሚለው ሲታከልበት መሆኑን እንዲገነዘብ አድርጎታል፡
፡ በሌላ አገላለጽ ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚነግረን ከሆነ እግዚአብሔር ትዳርን ሲሰጥ ዋና ዓላማው ልጅ መውለድ ቢሆን ኖሮ
ታላቅ ምስጢር የሆነውን ትዳር [በቤተክርስቲያን ውስጥ] መመስረት ባላስፈለገው ነበር፡፡ በመሆኑም የትዳር ዋና ዓላም ከዚህ
እጅግ የላቁ ነው፡፡ ይህም ደግሞ ልክ ማጣትን፣ ቅምጥልነትን እና ራስን ማጉደፍ ከመሰሉ ኃጢያቶች ለመራቅም ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በወንድ እና በሴት መካከል ያለው ኦርቶዶክሳዊ ኅብረት ታላቅ ምስጢር እንደሆነና፤ ይህም ኅብረት
ከእግዚብሔር የተሰጠ መሆኑን ይነግረናል44፡፡ ወንድ ልጅ ያሳደጉትን አባት እና እናቱን ትቶ ወደማያውቃት ሴት ዘንድ እንዲሄድ
መታዘዙ የትዳር ምሥጢር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ጠቋሚ አድርጎም ይወስደዋል45፡፡ በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል ያለውም
ጾታዊ መፈላለግ የዚህ ምስጢር አንድ ክፍል ሲሆን እንዲህ በማለትም ይጠቅሰዋል፡-

እነዚህ አንድ አካል ይሆናሉ፡፡ ይህ የፍቅር ምስጢር ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ አንድ አካል ባይሆኑና ለየብቻቸው ቢኖሩ
ልጆች ሊኖሯቸው አይችሉም፤ አንድ አካል ወደ መሆን ሲዋሐዱ ግን ልጆችን ይወልዳሉ፡፡ ከዚህ ምን መማር እንችላለን?
የዚህ ግንኙነት ጥንካሬ ታላቅ ኋይል እንዳለው እንማራለን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ገና ከፍጥረት ጅማሮ አንዱን ሁለት
አድርጎ ከፈለ፣ ለየብቻቸውም በራሳቸው መራባት እንደማይችሉ ለማሳየት ለብቻቸው ልጆችን ለመውለድ በቂ
እንዳይሆኑ አደረጋቸው፡፡ አንድ ሳይሆኑ ለየብቻቸው ግማሽ ናቸውና ልክ እንደ ጥንተ-ተፈጥሮው ጊዜ ሁሉ ልጆችን
መውለድ አይቻላቸውም46፡፡
አዳም እና ሔዋን አስቀድመው አንድ እንደነበሩት ሁሉ በትዳር ውስጥ ባል እና ሚስት አንድ ይሆናሉ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እንደሚነግረን ከሆነ ባል እና ሚስት በትዳር ከተዋሐዱ በኋላ ሁለት አካል ሳይሆኑ ቀድመው እንደነበሩት አዳም እና ሔዋን
ሁሉ አንድ አካል ናቸው47፡፡ እንደገናም ሴቷን ‹‹ረዳት›› ብሎ መጥራቱ (ዘፍ 2፡18-20) አንድ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው
ይላል48፡፡

አስቀድሞ የተገለጸውን ነጥብ ስንረዳ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ልጅን ስለመውለድ የተናገረውን ይዘን ኦሮቶዶክሳዊ ጋብቻ
የሚያጠነጥነው ዘር በመተካት ላይ ብቻ እንደሆነ አድርገን ልንረዳ አይገባም፡፡ልጆች ለመተካት ሁለቱም (ባልና ሚስት)

43
«Καὶ νῦν δὲ οὐχ ἡ τοῦ γάμου δύναμις τὸ γένος συγκροτεῖ τὸ ἡμέτερον ἀλλ' ὁ τοῦ κυρίου λόγος ὁ παρὰ τὴν ἀρχὴν
εἰπών· “Αὐξάνεσθαι καὶ πληθύνεσθαι καὶ πληρώσατε τὴν γῆν.” Τί γάρ, εἰπέ μοι, τὸν Ἀβραὰμ εἰς παιδοποιΐαν τὸ
πρᾶγμα ὤνησεν; Οὐκ ἐπὶ τοσούτοις αὐτῷ χρησάμενος ἔτεσι ταύτην ὕστερον ἀφῆκε τὴν φωνήν· “∆έσποτα, τί μοι
δώσεις; Ἐγὼ δὲ ἀπολύομαι ἄτεκνος;”»De Virginitate, Paragraph 15. Translation in Miller, Women, 110.
44
«δεσµὸς ὡρισµένος παρὰ Θεοῦ.» In Epistulam ad Colossenses, Homily 12.
45
«Ὄντως γὰρ, ὄντως μυστήριόν ἐστι, καὶ μέγα μυστήριον, ὅτι τὸν φύντα, τὸν γεννησάμενον, τὸν ἀναθρεψάμενον,
τὴν ὠδινήσασαν, τὴν ταλαιπωρηθεῖσαν ἀφεὶς, τοὺς τὰ τοσαῦτα εὐεργετήσαντας, τοὺς ἐν συνηθείᾳ γενομένους, τῇ
μηδὲ ὀφθείσῃ, μηδὲ κοινόν τι ἐχούσῃ πρὸς αὐτὸν προσκολλᾶται, καὶ πάντων αὐτὴν προτιμᾷ. Μυστήριον ὄντως
ἐστί.Καὶ οἱ γονεῖς τούτων γινομένων οὐκ ἄχθονται, ἀλλὰ μὴ γινομένων μᾶλλον· καὶ χρημάτων ἀναλισκομένων καὶ
δαπάνης γινομένης, ἥδονται.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
46
«Ἔρχονται ἓν σῶμα γενησόμενοι.Ἰδοὺ πάλιν ἀγάπης μυστήριον. Ἂν οἱ δύο µὴ γένωνται ἓν, οὐκ ἐργάζονται
πολλοὺς, ἕως ἂν δύο µένωσιν· ὅταν δὲ εἰς ἑνότητα ἔλθωσι, τότε ἐργάζονται.Τί µανθάνοµεν ἀπὸ τούτου; Ὅτι πολλὴ
τῆς ἑνώσεως ἡ ἰσχύς. Τὸ εὐµήχανον τοῦ Θεοῦ τὸν ἕνα εἰς δύο διεῖλε παρὰ τὴν ἀρχὴν, καὶ θέλων δεῖξαι ὅτι µετὰ τὸ
διαιρεθῆναι καὶ εἷς µένει, οὐκ ἀφῆκεν ἕνα ἀρκεῖν πρὸς τὴν γέννησιν. Οὐ γάρ ἐστιν εἷς [ὁ] οὐδέπω, ἀλλ' ἥµισυ τοῦ
ἑνός· καὶ δῆλον, ὅτι οὐ παιδοποιεῖ, καθάπερ καὶ πρότερον.» InEpistulam ad Colossenses, Homily 12.Translation with
reference to the modern Greek in Παιδαγωγική, p. 22
47
«Γυνὴ γὰρ καὶ ἀνὴρ οὐκ εἰσὶν ἄνθρωποι δύο, ἀλλ' ἄνθρωπος εἷς.» In Epistulam ad Colossenses, Homily 12.
48
«∆ιὰ τοῦτο καὶ βοηθὸν καλεῖ, ἵνα δείξῃ ὅτι ἕν εἰσι.» In Epistulam ad Colossenses, Homily 12.
ማስፈለጋቸው በመካከላቸው ያለው የጥልቅ ትስስራቸው ከፍተኛ መገለጫ ብቻ ነው፡፡ የዚህን ትስስር ጥንካሬንም እንዲህ ሲል
ጠቅሶታል፡-

መዝሙረኛው ዳዊት እጅግ በሚወደው በዮናታን ሞት ምክንያት ሐዘኑን ሲገልጽ የፍቅራቸውን ኃያልነት ለማሣየት
የተጠቀመው ቃል ምን ነበር? ‹‹…ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበር›› [1 ሳሙ 1፡26] የሚል ነው፡፡ በወንድ
እና በሴት መካከል ያለው ፍቅር ከስሜቶች ሁሉ ኃያል ነው፡፡ ሌሎች ስሜቶች ምንም ኃያል ቢሆኑም ስንኳ ይህ
ስሜት ግን ከሌሎች በተለየ መልኩ የማይጠፋ ጽኑ እና በሁለቱ የተቃራኒ ጾታዎች ውስጥ በጥልቀት የተተከለ ነው፡፡
እኛ ልብ ባንለው ስንኳ ከመካከላችን ሆኖ ወንዶችን እና ሴቶችን አንዳቸውን ወደ አንዳቸው ይስባል - የዚህም
ምክንያት በመጀመሪያ ሴት ከወንድ በመገኘቷ እና ከወንድ እና ከሴት ደግሞ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ስለሚገኙ
ነው49፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በወንድና በሴት መካከል ያለው የፍቅር ኃይል የተመሰለው አዳም የገዛ አካሉ ከሆነችው ከሔዋን ጋር
እንዲዋሐድ ከመሰጠቱ ጋር መሆኑን ያብራራል(ዘፍ 3፡24)50፡፡ ይህ ከመጀመርያ ጀምሮ የነበረ አንድነት የተነሣው በሁለት
ቀድሞ በማይገናኙ (አንድ ባልነበሩ) ወንድና ሴት መካከል ያለውን የተቃራኒ ጾታ ፍቅር ጥንካሬ ለማሳየት ነው፡፡የዚህ በባልና
ሚስት መካከል ያለ ፍቅርና አካላዊ ውሕደት መረበሽ ትዳሩን ሊበጠብጠው ይችላል፡፡ ይህም በተለየ ግልጽ የሚሆነው ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ ክርስቲያን ካልሆነ ሰውና ዘማዊ ከሆነ ሰው ጋር የመጋባት ውጤት ምን እንደሚመስል በማነጻጸር
ያስቀመጠውን ስንመለከት ነው፡፡ አንድ ሰው ክርስቲያን ያልሆነ ሰውን ቢያገባ ትዳሩን አይፍታ ምክንያቱም የአንዳቸው ክርስትና
ሌላኛውን ይቀድሰዋልና ፤ ዘማዊ የሆነ ሰው ያገባ እንደሆነ ግን ትዳሩን ሊያጠፋው (ሊያፈርሰው) ይችላል ይላል51፡፡ ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ ይሄንን ያለው በእንደዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለማውገዝ አይደለም፤ ምክንያቱም በጸጸት
ከተመለሱ ንስሓ የትኛውንም ኃጢአት ይቅር ያስብላልና ፤ ነገር ግን እንዲህ ማለቱ የጋብቻ ትስስር ጥንካሬ ወይም ኃይል ያለው
በትዳሩ የአካላዊ ውሕደት ጥንካሬ ላይ መሆኑን ለማጠየቅ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የባለ ትዳሮች ውሕደት በቤተክርስቲያን በኩል መሆን እንዳለበትም በአጽንኦት ይናገራል፡፡ ይህንንም
በተመለከተ ‹‹በሥጋዊ ፍላጎት ወይም በአንዳቸው አስገዳጅነት ሳይሆን በክርስቶስ የሆነ መንፈሳዊ ጋብቻ ትክክለኛ ጋብቻና
መንፈሳዊ ልደት ነው፡፡››52 ይላል፡፡ ጋብቻን መንፈሳዊ ልምምድ ለማድረግ ጋብቻው ወደ ድኅነት የሚወስድ ምሥጢረ
ቤተክርስቲያን መሆኑን መረዳትና ከትዳር አጋር ጋር ከእግዚአብሔር በተሰጠ ሓላፊነት ድኅነቱን ገንዘብ ለማድረግ በጋራ አብሮ
መኖር መሆኑን አምኖ መቅረብ ያስፈልጋል ፡፡ በወንጌል ትርጓሜው ላይ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ትዳር ግዴታዎች በዝርዝር

49
«∆ιὰ τοῦτο καί τις τὴν ὑπερβάλλουσαν ἀγάπην δηλῶν µακάριος ἀνὴρ, καί τινα τῶν αὐτῷ φίλων καὶ ὁµοψύχων
πενθῶν, οὐ πατέρα εἶπεν, οὐ µητέρα, οὐ τέκνον, οὐκ ἀδελφὸν, οὐ φίλον, ἀλλὰ τί; Ἔπεσεν ἐπ' ἐµὲ ἡ ἀγάπησίς σου,
φησὶν, ὡς ἀγάπησις τῶν γυναικῶν. Ὄντως γὰρ, ὄντως πάσης τυραννίδος αὕτη ἡ ἀγάπη τυραννικωτέρα.Αἱ μὲν γὰρ
ἄλλαι, σφοδραί· αὕτη δὲ ἡ ἐπιθυμία ἔχει καὶ τὸ σφοδρὸν, καὶ τὸ ἀμάραντον. Ἔνεστι γάρ τις ἔρως ἐμφωλεύων τῇ
φύσει, καὶ λανθάνων ἡμᾶς συμπλέκει ταῦτα τὰ σώματα. ∆ιὰ τοῦτο καὶ ἐξ ἀρχῆς ἀπὸ ἀνδρὸς ἡ γυνὴ, καὶ μετὰ ταῦτα
ἀπὸ ἀνδρὸς καὶ γυναικὸς ἀνὴρ καὶ γυνή.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Roth and Anderson, St.
John Chrysostom, 43-44 with underlined alterations.
50
«“Ὁρᾷς σύνδεσμον καὶ συμπλοκὴν, καὶ πῶς οὐκ ἀφῆκεν ἑτέραν ἐπεισελθεῖν οὐσίαν ἔξωθεν; Καὶ ὅρα πόσα
ᾠκονόμησε. Τὴν ἀδελφὴν ἠνέσχετο γαμῆσαι αὐτὸν τὴν αὑτοῦ, μᾶλλον δὲ οὐ τὴν ἀδελφὴν, ἀλλὰ τὴν θυγατέρα,
μᾶλλον δὲ οὐ τὴν θυγατέρα, ἀλλά τι πλέον θυγατρὸς, τὴν σάρκα τὴν αὑτοῦ.Τὸ δὲ ὅλον ἐποίησεν ἄνωθεν, ὥσπερ ἐπὶ
τῶν λίθων, εἰς ἓν αὐτοὺς συνάγων.» Translation in Roth and Anderson, St. John Chrysostom, 43-44.
51
«Πῶς γὰρ ἡ τὸν ἔμπροσθεν ἀτιμάσασα χρόνον, καὶ γενομένη ἑτέρου, καὶ τοῦ γάμου τὰ δίκαια ἀφανίσασα,
ἀνακαλέσασθαι δυνήσεται τὸν ἠδικημένον, πρὸς τούτοις καὶ τὸν μένοντα ὡς ξένον; Πάλιν ἐκεῖ μὲν μετὰ τὴν πορνείαν
ὁ ἀνὴρ οὐκ ἔστιν ἀνήρ· ἐνταῦθα δὲ, κἂν εἰδωλολάτρις ἡ γυνὴ, τοῦ ἀνδρὸς τὸ δίκαιον οὐκ ἀπόλλυται.» In Epistulam i
ad Corinthios, Homily 19.Translation in Schaff, NPNF1-12, 189.
52
«Ἄρα γάμος ἐστὶν οὗτος γινόμενος κατὰ Χριστὸν, γάμος πνευματικὸς καὶ γέννησις πνευματικὴ, οὐκ ἐξ αἱμάτων,
οὐκ ἐξ ὠδίνων.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Schaff, NPNF1-13, 274.
ሲያብራራ በዋናነት በቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ ሚስቶች ሆይ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተክርስቲያን
ራስ እንደሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና››53 በሚለው ትዕዛዝ ላይ በመንተራስ ነው፡፡(ኤፌ 5፡
22-23) ከዚህ ጥቅስ በመነሣት ሚስቶች ለባሎቻቸው ልክ ቤተክርስቲያን ራሷ ለሆነው ለክርስቶስ የምታሳየውን ዓይነት ቅዱስ
የሆነ ፍራቻና አክብሮት እንዲያሳዩ መጠየቃቸውን (ጠ ጠብቆ ይነበብ) ያብራራል፡፡ በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ይሄ ፍራቻ ዓለማዊ
ከሆነ በዛቻ ከሚመጣ ወይም አንድ ሰው በኃጢአቱ ወይም በጥፋቱ ምክንያት ከሚመጣበት ፍራቻ ፍጹም የተለየ ከፍቅር ጋር
ብቻ የተሳሰረ የፍቅር ፍራቻ ነው፡፡54 የፔንታፖሊሱ (አምስቱ ከተሞች) ሊቅ ኔክታርዮስ እንዳለው ‹‹ይሄ ፍራቻ እንደ ስሜትነቱ
ከፍቅር ጋር የተሳሰረሲሆን በሴቷ ነፍስ ውስጥ የባል አክብሮትን የሚፈጥርና ካላቸው ጥብቅ ቁርኝት የተነሣ ባሏን ወደ
አለማክበር ደረጃ እንዳትደርስ የሚጠብቃት ነው፡፡››55

ይሄን ዐሳብ የበለጠ ለማጠንከር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ውስጥ የባልን ሓላፊነት ያስረዳበትን በቅርበት (በአጽንኦት)
መመልከት ጠቃሚ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሚስት ባሏን ታክብር ከሚለው ሓላፊነት በበለጠ የወንድ ሓላፊነት ጥልቅና
ከባድ ነው ይላል፡፡

ምሳሌውን ገና አልጨረሰምና አሁን ደግሞ ካንተ ምን ሌላ ነገር እንደሚፈልግ ስማ ‹‹ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ
ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ›› ብሏልና፡፡(ኤፌ 5፡25-26) ቀደም ብለን በሴቶች በኩል
የሚፈለገውን የአክብሮት መጠን አይተናል፤ አሁን ደግሞ ስለ ፍቅር መጠን ስማ፡፡ ልክ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ
እንደምትገዛለት ሚስትህ ላንተ እንድትገዛልህ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ልክ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን እንደሚያደርገው
ሁሉ አንተም ሚስትህን ለመውደድና ለመንከባከብ ሓላፊነቱን መውሰድ አለብህ፡፡ ስለ ሚስትህ ስትል ማንኛውንም
ዓይነት ስቃይና መከራ ሞትም ቢሆን ለመቀበል አታቅማማ፡፡ ይሄን ሁሉ አድርገህም ግን ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን
ያደረገላትን ያከል ለሚስትህ ልታደርግላት አትችልም፡፡56

ይሄ ዐሳብ በድጋሚ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ወንድ ራስነት ባብራራበት የኤፌሶን መልእክት ትርጓሜ ላይ ተነሥቷል፡፡
ሰባኪው እዚህም ጋር በድጋሚ በትዳር ውስጥ በወንድና በሴት መካከል ያለውን ግንኙነት በክርስቶስና በቤተክርስቲያን መካከል
ባለው ግንኙነት ምሳሌ ያስረዳል57፡፡ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ነፍሱን በፈቃዱ አሳልፎ እንደሰጣት ሁሉ ባልም የትዳር አጋሩ

53
«Αἱ γυναῖκες, τοῖς ἰδίοις ἀνδράσιν ὑποτάσσεσθε, ὡς τῷ Κυρίῳ, ὅτι ὁ ἀνήρ ἐστι κεφαλὴ τῆς γυναικὸς, ὡς καὶ ὁ
Χριστὸς κεφαλὴ τῆς Ἐκκλησίας, καὶ αὐτός ἐστι σωτὴρ τοῦ σώµατος.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
54
“‘And the wife see that she reverence her husband- Ἡ δέ γυνή ἵνα φοβῆται τόν ἄνδρα’: A theological commentary
on Ephesians 5:33 by Saint Nektarios, Metropolitan of Pentapolis, 1902,” republished and translated in English by
OODE, June 22, 2011,
http://www.oodegr.com/english/ekklisia/pateres/Saint_Nektarios_on_woman_respecting_man.htm
55
“‘And the wife see that she reverence her husband…” OODE, June 22, 2011.
56
«Ἀλλ' ἄκουσον, ἃ καὶ παρὰ σοῦ ἀπαιτεῖ· πάλιν γὰρ τῷ αὐτῷ κέχρηται ὑποδείγματι· Οἱ ἄνδρες, ἀγαπᾶτε, φησὶ, τὰς
γυναῖκας ἑαυτῶν, καθὼς καὶ ὁ Χριστὸς ἠγάπησε τὴν Ἐκκλησίαν. Εἶδες μέτρον ὑπακοῆς; Ἄκουσον καὶ μέτρον ἀγάπης.
Βούλει σοι τὴν γυναῖκα ὑπακούειν, ὡς τῷ Χριστῷ τὴν Ἐκκλησίαν; Προνόει καὶ αὐτὸς αὐτῆς, ὡς ὁ Χριστὸς τῆς
Ἐκκλησίας· κἂν τὴν ψυχὴν ὑπὲρ αὐτῆς δοῦναι δεῖ, κἂν κατακοπῆναι μυριάκις, κἂν ὁτι οῦν ὑπομεῖναι καὶ παθεῖν, μὴ
παραιτήσῃ· κἂν ταῦτα πάθῃς, οὐδὲν οὐδέπω πεποίηκας, οἷον ὁ Χριστός.» In Epistulam ad Corinthios, Homily 18.
Translation in Roth and Anderson, St. John Chrysostom, 46.
57
«Ὑποθώμεθα οὖν τὸν μὲν ἄνδρα ἐν τάξει κεῖσθαι κεφαλῆς, τὴν δὲ γυναῖκα ἐν τάξει σώματος.Εἶτα καὶ ἀπὸ λογισμῶν
δεικνὺς. Ὅτι ὁ ἀνὴρ κεφαλή ἐστι τῆς γυναικὸς, φησὶ, καθὼς καὶ ὁ Χριστὸς τῆς Ἐκκλησίας, καὶ αὐτός ἐστι σωτὴρ τοῦ
σώματος. Ἀλλ' ὡς ἡ Ἐκκλησία ὑποτάσσεται τῷ Χριστῷ, οὕτω καὶ αἱ γυναῖκες τοῖς ἰδίοις ἀνδράσιν ἐν παντί. Εἶτα, Ὁ
ἀνήρ ἐστιν, εἰπὼν, κεφαλὴ τῆς γυναικὸς, ὡς καὶ ὁ Χριστὸς τῆς Ἐκκλησίας, καὶ αὐτός ἐστι σωτὴρ, ἐπάγει, τοῦ σώματος·
καὶ γὰρ ἡ κεφαλὴ τοῦ σώματος σωτηρία ἐστίν.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Roth and
Anderson, St. John Chrysostom, 45.
እንድትሆን ለመረጣት ለሚስቱ ይሄንን በጥቂቱ ስንኳ ሊያደርግላት ይገባል58፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በድጋሚ እንዲህ ይላል፡
- “ሕይወትህን ስንኳ ለሚስትህ አሳልፈህ መስጠትህ አስፈልጊ ቢሆን፣ ዐሥር ሺ ጊዜ መቆራረጥ ቢኖርብህ፣ የትኛውንም ዓይነት
ስቃይና መከራ መቋቋም ቢጠበቅብህ ወደኋላ አትበል፡፡ ይሄን ሁሉ አድርገህም ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ያደረገላትን ጥቂቱን
ስንኳ ልታደርግ አትችልምና59፡፡”

በሌላ አገላለጽ ባል በትዳር ላይ የተሰጠው ራስነት ለሚስቱ ፍቅርና እንክብካቤ ካልሰጠ ሊሟላ አይችልም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ በእርሱ ዘመን ወንድ የበላይ በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ አንደነበረው ልማድ ወንድ ይሄን በትዳር ላይ ያለውን
የራስነት ሥልጣን አለአግባብ ባይጠቀምና ለሚስቱ ፍቅርና እንክብካቤ ቢቸር የሚያገኘው የተለየ ጥቅም ምንድነው? ለሚለው
ጥያቄ ሲመልስ ባልና ሚስት ከትዳር በኋላ ለሚኖራቸው አንድ አካል60 ባል ራስ ሲሆን ሚስት ደግሞ አካል ናት፤ ባል (ራስ)
አካሉን (ሚስትን) ከጠላ አብሮ ይጠፋል61 ምክንያቱም ራስ ያለ አካል ሊኖር አይችልምና፡፡ስለዚህ እንዲህ ብሎ ይመክራል፡-
“ባል ሚስት ለምታሳየው አክብሮት ተመጣጣኝ የሆነ ፍቅር ይስጣት62፡፡”

ምንም ስንኳ ባሎች ለሚስቶቻቸው ተንከባካቢና በመንፈሳዊ ጉዳይ አስተማሪዎቻቸው እንዲሆኑ ቢጠይቅም የትዳር ግንኙነቱ
ግን በሁለቱም እኩልነት ላይ የተመሠረት የሚስት ክብር ከባል ክብር ጋር በእኩል የሚታይበት መሆን እንዳለበት ያስተምራል63፡
፡ ይሄንንም ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የላከውን መልእክት በተረጎመበት ድርሳኑ አስረድቷል64፡፡ ሚስት ለባሏ ጌታም
ባሪያም እንደሆነችው ሁሉ ባልም ለሚስቱ ጌታና ባሪያ ነው፡፡ ስለዚህ አንዳቸው በሌላኛው ላይ ራሳቸውን የበላይ አድርገው
መመልከት የለባቸውም ፤ማናቸውም የበላይ ማናቸውም የበታች አይደሉም ፤ ይልቅስአንዳቸው በአንዳቸው ላይ የተመሠረቱ
እኩል ባለሥልጣናት ናቸው፡፡ ይሄ አጽንኦት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ትዳር ውስጥ የሚገባ ሰው የትዳር
አጋሩ አገልጋይ መሆን ስላለበት ደቀመዛሙርቱ ቢቻል ከማግባት እንዲከለከሉ የጻፈውን (1ኛ ቆሮ 7፡32-35) ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ ሲተረጉም እንዲ ብሏል፡-

በዚህ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዛሙርቱን ከትዳር ሊያርቃቸው ይፈልጋል፡፡ ከትዳር በኋላ ለሚስትህ ፈቃድ የምትገዛ
እንጂ የራስህ ጌታ እንደማትሆን ስታውቅ በዚህ ሓላፊነት (ትዳር) ውስጥ ላለማለፍ ትፈልጋለህ ምክንያቱም አንዴ ወደ
ትዳር ከገባህ እስከ መጨረሻው ሚስትህን ለማስደሰት ባሪያ መሆንህ ነውና፡፡65

58
«Τί δὲ λέγω; καὶ μωρὰ ἦν, καὶ βλάσφημος· ἀλλ' ὅμως τοσούτων ὄντων, ὡς ὑπὲρ ὡραίας, ὡς ὑπὲρ ἀγαπωμένης, ὡς
ὑπὲρ θαυμαστῆς, οὕτως ἑαυτὸν ἐξέδωκεν ὑπὲρ τῆς ἀμόρφου. Καὶ τοῦτο θαυμάζων ὁ Παῦλος ἔλεγε· Μόλις γὰρ ὑπὲρ
δικαίου τις ἀποθανεῖται· καὶ πάλιν, Εἰ ἔτι ἁμαρτωλῶν ἡμῶν ὄντων ὁ Χριστὸς ὑπὲρ ἡμῶν ἀπέθανε.Καὶ τοιαύτην
λαβὼν, καλλωπίζει αὐτὴν καὶ λούει, καὶ οὐδὲ τοῦτο παραιτεῖται.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in
Scaff, NPNF1-13, 270.
59
«Kἂν τὴν ψυχὴν ὑπὲρ αὐτῆς δοῦναι δεῖ, κἂν κατακοπῆναι μυριάκις, κἂν ὁτιοῦν ὑπομεῖναι καὶ παθεῖν, μὴ
παραιτήσῃ· κἂν ταῦτα πάθῃς, οὐδὲν οὐδέπω πεποίηκας, οἷον ὁ Χριστός,» In Epistulam ad Ephesios, Homily
20.Translation in Schaff, NPNF1-13, 269.
60
«σώμα» የሚለው ‹አካል› ተብሎ ይተረጎማል፡፡
61
«κἂν καταφρονῇ τοῦ σώματος ἡ κεφαλὴ, καὶ αὐτὴ προσαπολεῖται·» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
62
«ἀλλ' ἀντίῤῥοπον τῆς ὑπακοῆς εἰσαγέτω τὴν ἀγάπην.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
63
የግሪኩ ቃል «ἰσοτιµία» የሚለው ሲሆን ‘ἶσος’ እና ‘τιμή,’ ከተሰኙ ሁለት ቃላት የተገኘ ነው፡፡ የመጀመሪያው ቃል ትርጉም ‹እኩል› ማለት ሲሆን
የሁለተኛው ደግሞ ‹ክብር› የሚል ነው፡፡
64
In Epistulam ad Corinthios, Homily 18.
65
«αὐτοῖς τοῖς περὶ τοῦ γάμου λόγοις ἐξαγαγεῖν αὐτοὺς τοῦ γάμου βουλόμενος. Ὁ γὰρ ἀκούσας ὅτι μετὰ τὸν γάμον
οὐκ ἔσται κύριος ἑαυτοῦ ἀλλ' ἐν τῇ τῆς γυναικὸς κείσεται γνώμῃ ταχέως ἀπαλλαγῆναι σπουδάσει τῆς πικροτάτης
δουλείας, μᾶλλον δὲ μηδὲ τὴν ἀρχὴν τὸν ζυγὸν ὑπελθεῖν, ἐπειδὴ εἰσελθόντα ἅπαξ δουλεύειν ἀνάγκη λοιπὸν ἕως ἂν
τῇ γυναικὶ τοῦτο δοκῇ.» De Virginitate, Homily 18. Translation in Miller, Women, 114.
ይሄ ማለት ምንም ስንኳ በሴትና በወንድ መካከል የሥልጣን ተዋረድ ልዩነት ቢኖርም ባል ለሚስቱ በማንኛውም ጉዳይ ላይ
አገልጋይዋ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የትዳራቸውን ክብርና አንዳቸው የአንዳቸውን ክብር ማስጠበቅ ላይ ደግሞ ሁለቱም እኩል
ሓላፊነት አለባቸው፡፡ በተመሳሳይ ውሕደታቸውን ሊጎዳ በሚችለው በዝሙት ኃጢአት መውደቅ ሁለቱንም እኩል የሚያስገስጽ
ነው66፡፡

ምንም ስንኳ ባልና ሚስት ከትዳር በኋላ የሚኖራቸው የአንዱ አካል ራስና አካል ተብለው ቢገለጹም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አንድም ቦታ ጾታዊ የሓላፊነት ክፍፍሎች መለኮታዊ ዕቅድ ናቸው አለማለቱ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ሚስቶች ለባሎቻቸው ውሳኔ
እንዲታመኑና በመንፈሳዊ ጉዳይ መሪዎቻቸው እንደመሆናቸው እንዲያከብሯቸው ቢታዘዙም የጾታ ክፍፍል ያለበት የሕይወት
መንገድ በአስተምህሮ መልክ በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ውስጥ የለም፡፡ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሴቶችን ለቤት (ለጓዳ) ሥራዎች
ሓላፊ እያደረገ የተናገረበት ቦታ ሲኖር በዛ መልክ ለተከፋፈለ ማኅበረሰብ እየተናገረ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትርጓሜዎቹ በባለትዳሮች መካከል የሚኖረውን ጾታዊ ግንኙነት ሳይነካው አላለፈም፡፡
ኦርቶዶክሳዊውን ትውፊት በማንሣት ባልናሚስት በሚኖራቸው የተራክቦ ውሕደት አንድ ሥጋ እንደሚሆኑ ያስረዳል፡፡ በተራክቦ
ወቅት ሴቷ የወንዱን ዘር ትቀበልናበፍቅር መግባ ልጅ ታስገኛለች67፡፡ የሚወለደው ልጅ ደግሞ በወላጆቹ መካከል ድልድይ
ይሆናል፤ አንድነቱንም ያጠነክራል፡፡ እዚህ ጋር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የባልና የሚስትን አካላዊ ውሕደት ከአማኞች በሥጋ
ወደሙ አማካኝነት ከክርስቶስ አካል ጋር ከመዋሐድ ጋር ያመሳስለዋል68፡፡ ይሄ አገላለጽ ግን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር
ውስጥ ያለ ተራክቦ ልጅ ለመውለድ ብቻ የሚደረግ ነው ማለቱ እንዳልሆነ፤ ይልቅስ ልጅ በባለትዳሮቹ መካከል ያለ የፍቅር
ግንኙነት ፍሬ መሆኑን ለማጠየቅ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሕይወትን እውነታዎች ያለማፈር በግልጽ ያስቀምጥ ነበር፡፡ የጋብቻ መኝታው ክቡርና ቅዱስ መሆኑን
በማስረዳት ከጾታዊ (ከተራክቦ) ውይይት የሚሸሹ ምእመናንን ይወቅስም ነበር፡፡ በጋብቻ የሚደረግ ተራክቦ አለአግባብ
ማኅበራዊ ሥነ ምግባሮችን በጣሰ መንገድ እስካልተደረገ ድረስ ነውር የለበትም ይላል፡፡ ከዚህም ትዳር መንፈሳዊ የጋራ ጉዞ
እንጂ በራሱ መድረሻ ወይም መጨረሻ አለመሆኑን በማሰብ የሚከናወን መሆን አለበት ማለቱን እንጂ በትዳር ውስጥ ያለን
ተራክቦ አለመቃወሙን እንመለከታለን፡፡ ትዳር መንፈሳዊ ዓላማውን እንዲያሳካ ክርስቶስን ራስ ያደረገ የሁለት ሰዎች (የወንድና
የሴት) መንፈሳዊ ትስስር መሆን አለበትና፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የትዳር መኝታው ክቡር ሲሆን አንዱ ዓላማውም ባለትዳሮቹ ከፍትወትና
ከዝሙት ፈተና ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማገዝ ነው፡፡ስለዚህም ምክንያት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያለ ጋራ ስምምነት ከተራክቦ
የሚታቀቡ ባለ ትዳሮችን ይቃወማል69፡፡ እንደርሱ ከሆነ ባለትዳሮች ከተራክቦ መታቀብ ያለባቸው ሁለቱም በጾምና በጸሎት

66
Roth and Anderson, St. John Chrysostom, 86.
67
«Πῶς δὲ καὶ γίνονται εἰς σάρκα µίαν; Καθάπερ χρυσοῦ τὸ καθαρώτατον ἂν ἀφέλῃς καὶ ἑτέρῳ ἀναµίξῃς χρυσῷ,
οὕτω δὴ καὶ ἐνταῦθα, τὸ πιότατον τῆς ἡδονῆς χωνευούσης ἡ γυνὴ δεχοµένη τρέφει καὶ θάλπει, καὶ τὰ παρ' ἑαυτῆς
συνεισενεγκαµένη ἄνδρα ἀποδίδωσι. Καὶ γέφυρά τίς ἐστι τὸ παιδίον. Ὥστε οἱ τρεῖς σὰρξ γίνονται µία, τοῦ παιδὸς
ἑκατέρωθεν ἑκατέρους συνάπτοντος.» In Epistulam ad Colossenses, Homily 12. Translation in Schaff, NPNF1-13, 569.
68
«…καὶ λοιπὸν ἡ σὰρξ ὁ πατὴρ καὶ ἡ μήτηρ καὶ ὁ παῖς ἐστιν ἐκ τῆς ἑκατέρου συνουσίας συγκραθεῖσα· καὶ γὰρ
μιγέντων τῶν σπερμάτων, τίκτεται ὁ παῖς· ὥστε τοὺς τρεῖς εἶναι μίαν σάρκα. Οὕτως οὖν ἡμεῖς πρὸς τὸν Χριστὸν
γινόμεθα μία σὰρξ διὰ μετουσίας· καὶ πολλῷ μᾶλλον ἡμεῖς, ἢ τὸ παιδίον. Τί δή ποτε; Ὅτι ἐξ ἀρχῆς οὕτω γέγονε.» In
Epistulam ad Ephesios, Homily 20. Translation in Schaff, NPNF1-13, 272.
69
«Μὴ ἀποστερεῖτε ἀλλήλους, εἰ µή τι ἂν ἐκ συµφώνου. Τί δὴ τοῦτό ἐστι; Μὴ ἐγκρατευέσθω, φησὶν, ἡ γυνὴ, τοῦ
ἀνδρὸς ἄκοντος, µήτε ὁ ἀνὴρ, τῆς γυναικὸς µὴ βουλοµένης. Τί δήποτε; Ὅτι µεγάλα ἐκ τῆς ἐγκρατείας ταύτης τίκτεται
κακά· καὶ γὰρ καὶ µοιχεῖαι καὶ πορνεῖαι καὶ οἰκιῶν ἀνατροπαὶ πολλάκις ἐντεῦθεν ἐγένοντο. Εἰ γὰρ ἔχοντες τὰς ἑαυτῶν
γυναῖκας, πορνεύουσι, πολλῷ µᾶλλον, ἂν αὐτοὺς τῆς παραµυθίας ταύτης ἀποστερήσῃς. Καὶ καλῶς εἶπε, Μὴ
ἀποστερεῖτε, ἀποστέρησιν ἐνταῦθα καὶ ὀφειλὴν ἀνωτέρω εἰπὼν, ἵνα δείξῃ τῆς δεσποτείας τὴν ἐπίτασιν. Τὸ γὰρ
ἄκοντος θατέρου ἐγκρατεύεσθαι θάτερον, ἀποστερεῖν ἐστι· τὸ δὲ ἑκόντος, οὐκέτι. Οὐδὲ γὰρ, εἰ πείσας µε λάβοις τι
τῶν ἐµῶν, ἀποστερεῖσθαί φηµι. Ὁ γὰρ ἄκοντος καὶ βιαζοµένου λαβὼν, ἀποστερεῖ· ὅπερ ποιοῦσι πολλαὶ γυναῖκες,
በተአቅቦ ለመቆየት ከተስማሙ ብቻ መሆን አለበት (ጾምና ጸሎቱን ግን ተራክቦን ባላቋረጡም ጊዜ መቀጠል አለባቸው)፡፡
በሁለቱም ፈቃድ የሚደረግ ካልሆነ ግን ፈቃደኛ ያልሆነውን አጋር ለዝሙትና ሌሎች ፈተናዎች ሊያጋልጠው ይችላል፤ ይሄ
ደግሞ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ቅድስና በጋራ የጀመሩትን ሕይወት(ጉዞ) ማደናቀፍ ነው፡፡

ትዳር በሁለት ፍቅረኛሞች መካከል በጋራ እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚፈጸም ኅብረት ቢሆንም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ካስተዋላቸው ልምዶች በመነሣት የትዳር ሕይወት ሁሌ ሰላማዊ ላይሆን እንደሚችልና ባለትዳሮቹም ራስ ወዳድ የሚሆኑበት
አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ይናገራል፡፡ ስለ ድንግልና ባብራራበት የወንጌል ትርጓሜው ትዳር እጅግ መታገስና መቻቻልን
ይሻል ይላል70፡፡ በአንድ አጋጣሚ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምእመናንን እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው ‹‹ባል ለዘብተኛ ቢሆንና ሚስት
ግን ተንኮለኛ ፣ ስም አጥፊ፣ ወረኛ፣ ቅንጡ…ወዘተ ብትሆንስ ? በተቃራኒው ደግሞ ሚስት ጭምትና መልካም ሆና ባል ደግሞ
ነውረኛ ግድ የለሽ ፣ የማያስተውል ፣ ትዕቢተኛ ፣ ግልፍተኛ፣ ቁስ ወዳጅና ተማቺ ቢሆንስ?71 ይሄንን ጥያቄ ሲመልስ አንዳቸው
የአንዳቸውን ድክመት ለመሸከም መሞከር እንዳለባቸውና መጥፎ ጸባያቸውን እንዲያርሙ በመምከርና በማገዝ ጥሩ መንፈሳዊ
ሰው ሊያደርጓቸው እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ ያስተማረውን በመድገም ነው፡፡ ከዚህ ነጻ የሚሆኑትም አንዳቸው በሞት ሲለዩ
ብቻ ነው ይላል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትዳር ውስጥ ትዕግሥትና መቻቻል ኦርቶዶክሳዊ ጸባይ መሆናቸውን ሲያነሣ ያለ ጾታዊ
ልዩነትለሁለቱም ጾታዎች እያለ መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል72፡፡ በትዳር ውስጥ ያለ የትዳር ጥቃት (በዚሁ ጽሑፍ ይሄን ቃል
የተጠቀምነው በትዳር ውስጥ የሚፈጸምን ጥቃት ሁሉ ለማመልከት ነው) ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ስለሆነ ሲያወግዝም ደግሞ ሁለቱንም
እንደሚመለከት በመጠቆም ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ሚስቶች ባሎቻቸውን በድህነት ምክንያት እንዳይወቅሱ ወይም

µείζονα τῆς δικαιοσύνης ἁµαρτίαν ἐργαζόµεναι, καὶ τῆς ἀσελγείας τοῦ ἀνδρὸς ὑπεύθυνοι γινόµεναι ταύτῃ, καὶ
διασπῶσαι πάντα. ∆εῖ δὲ πάντων προτιµᾷν τὴν ὁµόνοιαν, ἐπειδὴ καὶ πάντων τοῦτο κυριώτερον, καὶ εἰ βούλει, καὶ
ἐπὶ τῶν πραγµάτων αὐτὸ ἐξετάσωµεν. Ἔστω γὰρ γυνὴ καὶ ἀνὴρ, καὶ ἐγκρατευέσθω ἡ γυνὴ µὴ βουλοµένου τοῦ
ἀνδρός· τί οὖν, ἂν ἐκεῖνος ἐντεῦθεν πορνεύῃ, ἢ µὴ πορνεύῃ µὲν, ἀλγῇ δὲ καὶ θορυβῆται καὶ πυρῶται καὶ µάχηται,
καὶ µυρία τῇ γυναικὶ πράγµατα παρέχῃ; τί τὸ κέρδος τῆς νηστείας καὶ τῆς ἐγκρατείας, ἀγάπης διεῤῥηγµένης; Οὐδέν.
Πόσας γὰρ ἔνθεν λοιδορίας, πόσα πράγµατα, πόσον ἀνάγκη γίνεσθαι πόλεµον.» In Epistulam ad Corinthios, Homily
19. Translation in Schaff, NPNF1-12, 186-187.
70
«Ὅτι πολλὴ ἡ τοῦ γάμου δουλεία καὶ ἀπαραίτητος. Τί οὖν ἐὰν μὲν ὁ ἀνὴρ ἐπιεικὴς ᾖ, ἡ δὲ γυνὴ μοχθηρά, λοίδορος,
λάλος, πολυτελής, τὸ κοινὸν τοῦτο πασῶν αὐτῶν νόσημα, ἑτέρων πλειόνων γέμουσα κακῶν, πῶς οἴσει τὴν
καθημερινὴν ταύτην ἀηδίαν ἐκεῖνος ὁ δείλαιος, τὸν τῦφον. τὴν ἀναισχυντίαν; Τί δαί, ἂν τοὐναντίον αὐτὴ μὲν ᾖ
κοσμία καὶ ἥσυχος, ἐκεῖνος δὲ θρασύς, ὑπεροπτικός, ὀργίλος, πολὺν μὲν ἀπὸ τῶν χρημάτων, πολὺν δὲ ἀπὸ τῆς
δυναστείας ὄγκον περιβεβλημένος, καὶ τὴν ἐλευθέραν ὡς δούλην ἔχει καὶ τῶν θεραπαινίδων μηδὲν ἄμεινον πρὸς
αὐτὴν διάκειται, πῶς οἴσει τὴν τοσαύτην ἀνάγκην καὶ βίαν; Τί δαί, ἂν συνεχῶς αὐτὴν ἀποστρέφηται καὶ διὰ παντὸς
μένῃ τοῦτο ποιῶν; Καρτέρει, φησίν, πᾶσαν ταύτην τὴν δουλείαν· ὅταν γὰρ ἀποθάνῃ, τότε ἐλευθέρα ἔσῃ μόνον,
ζῶντος δὲ δυοῖν θάτερον ἀνάγκη, ἢ παιδαγωγεῖν αὐτὸν μετὰ πολλῆς τῆς σπουδῆς καὶ βελτίω ποιεῖν ἤ, εἰ τοῦτο
ἀδύνατον, φέρειν γενναίως τὸν ἀκήρυκτον πόλεμον καὶ τὴν ἄσπονδον μάχην.» De Virginitate, Paragraph 40.
71
«Τί οὖν ἐὰν μὲν ὁ ἀνὴρ ἐπιεικὴς ᾖ, ἡ δὲ γυνὴ μοχθηρά, λοίδορος, λάλος, πολυτελής…; Τί δαί, ἂν τοὐναντίον αὐτὴ
μὲν ᾖ κοσμία καὶ ἥσυχος, ἐκεῖνος δὲ θρασύς, ὑπεροπτικός, ὀργίλος, πολὺν μὲν ἀπὸ τῶν χρημάτων, πολὺν δὲ ἀπὸ τῆς
δυναστείας ὄγκον περιβεβλημένος…» De Virginitate, Paragraph 40.
72
በኦርቶዶክስ ትውፊት ዶግማና የነገረ መለኮት ጉዳይያልሆኑ የአባቶች ትምህርቶች እንደምክር ነው የሚወሰዱት፡፡ ስለዚህ ባሏ ክፉ የሆነባት አንዲት ሴት
ምን ታድርግ ለሚለው አንድ ወጥ የሆነ አቋም ላይኖር ይችላል፡፡ ይሄ በሴቷ የቤተሰብ አስተዳደር መርህና የምርጫ ውሳኔ ላይ የሚወሰን ነው፡፡
እንዳይሰድቡ73፤ ባሎችም በሚስቶቻቸው መከበርን በኃይልና በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅርና በመልካም ጠባይ ለያገኙት
እንደሚገባ74 መምከሩ ነው፡፡ እንዲህ በማለት፡-

… ባል ይሄንን ሲሰማ ሥልጣን ስላለው (የሚስቱ ራስ ስለሆነ) ሚስቱን መስደብና መጉዳት የለበትም ይልቅስ
ለመልካም ነገር ሊያበረታታት ፣ ሊመክራትና ሊያግዛት ይገባል፤ እንደገናም በንግግር ሊያሳምናት እንጂ እጁን
ሊያነሣባት አይገባም፡፡ እነዚህ ሁሉ አንድ መንፈሳዊ ከሆነ ሰው መራቅ ያለባቸው ሲሆኑ፤ ከኩራት፣ ከስድብ፣
ከማሸማቀቅና ከማቃለል ይልቅ መምከር፣ ማገዝና መርዳት አለበት፡፡75

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወንዶች መንፈሳዊ ሥልጣናቸውን አለአግባብ እንዳይጠቀሙ ያስጠነቅቃል ምክንያቱም በዓለም
ትብታብ ካልታሰረና በሃይማኖት ከሚኖር ወንድ ይሄ የማይጠበቅ በመሆኑ ነው፡፡ ትክክለኛ ባል ቅንና ታጋሽ፣ ለሚስቱ
ሲመልስላትም በጥንቃቄ በተሰደሩና መንፈሳዊ መረዳትን በሚጨምሩ መካሪ ቃላት መሆን አለበት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሴቶችን ከጥቃት ለመጠበቅ ያለውን ጽኑ አቋም ያረጋገጠው ሚስቶች ምንም ስንኳ የሚያናድድና
ለትችት የሚዳርግ ነገር ቢኖራቸውም ባሎች ታጋሽ፣ መልካምና ለፍርድ የማይቸኩሉ እንዲሆኑላቸው በማዘዙ ነው፡-

አንድ ሰው ባሪያውን በማስፈራራት ሊገዛው ይችል ይሆናል፤ አኔ ግን አይሆንም እላለሁ ምክያቱም ያ ባርያ አንድ ቀን
ከታሰረበት ሰንሰለት አምልጦ ሊጠፋ ይችላል፡፡ እንግዲህ አንድ ሰው ባሪያውን ስንኳ በጉልበት መግዛት ካልቻለ
የሕይወቱን አጋር ሚስቱን ፣ የልጆቹን እናት፣ የደስታውን ምንጭ በጉልበትና በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅርና በደስታ
ሊያኖራት ይገባል፡፡ ሚስት ባልን የምትፈራው ከሆነ ምን ዓይነት ትዳር ይኖራቸዋል? ባልስ እንደባርያ ከሚያኖራትና
ነጻነት ከሌላት ሚስቱ ምን ዓይነት ደስታን ሊያገኝ ይችላል? ስለ እርሷ መከራ ቢደርስብህ ስንኳ ልትወቅሳት አይገባም
ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ላይ ይሄን አላደረገምና፡፡76

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድ ሰው በባርያው የሚፈራው መፈራትና ባል ነጻ ፈቃድ ባላት ሚስቱ የሚፈራው መፈራት መካከል
ግልጽ የሆነ ልዩነት ያስቀምጣል፡፡ የሚስት ፍራቻ የአክብሮት ነው፡፡ ይሄም አክብሮት ባሏ ለእርሷ ከሚኖረው መልካም
አመለካከት፣ ከሚናገራት መልካም ንግግሮች እና ከሚያሳያት መልካም አካላዊ ምላሾች የሚመነጭ ነው፡፡ ባል ሚስቱን
ከመውቀስ ተከልክሎ ስለሚስቱ መከራን አንዲቀበል በዚህም ክርስቶስን አንዲመስል በትዳር ውስጥ ያለውን ኅብረት
በቤተክርስቲያንና በክርስቶስ መካከል ባለው ኅብረት እየመሰለ ያሳስባል፡፡ ይሄንንም በተለያዩ ቦታዎች ላይ አጽንኦት ሰጥቶ

73
«Μὴ λεγέτω ταῦτα γυνὴ, καὶ τὰ τούτοις ὅμοια· σῶμα γάρ ἐστιν, οὐχ ἵνα διατάττῃ τῇ κεφαλῇ, ἀλλ' ἵνα πείθηται καὶ
ὑπακούῃ. Πῶς οὖν οἴσει, φησὶ, τὴν πενίαν; πόθεν εὑρήσει παραμυθίαν; Ἐκλεγέσθω παρ' ἑαυτῇ τὰς πενεστέρας,
ἀναλογιζέσθω πόσαι πάλιν εὐγενεῖς καὶ ἐξ εὐγενῶν κόραι οὐ μόνον ἐξ ἀνδρῶν οὐδὲν προσέλαβον, ἀλλὰ καὶ
προσέδωκαν, καὶ τὰ αὐτῶν ἅπαντα ἀνάλωσαν· ἐννοείτω τοὺς ἐκ τοιούτων πλούτων κινδύνους, καὶ τὸν ἀπράγμονα
ἀσπάσεται βίον.Καὶ ὅλως εἰ φιλοστόργως πρὸς τὸν ἄνδρα διακέοιτο, οὐδὲν τοιοῦτον ἐρεῖ, ἀλλ' αἱρήσεται πλησίον
αὐτῆς ἔχειν αὐτὸν μηδὲν πορίζοντα, ἢ μυρία τάλαντα χρυσοῦ μετὰ μερίμνης καὶ φροντίδος τῆς ἐκ τῶν ἀποδημιῶν
ταῖς γυναιξὶν ἐγγινομένης ἀεί.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20. Translation in Schaff, NPNF1-13, 278-279.
74
«οὐ φόβῳ καὶ ἀπειλαῖς δεῖ καταδεσμεῖν, ἀλλ' ἀγάπῃ καὶ διαθέσει.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
Transaltion in Schaff, NPNF1-13, 270.
75
«Ἀλλὰ μηδὲ ὁ ἀνὴρ ταῦτα ἀκούων ὡς ἀρχὴν ἔχων, ἐπὶ ὕβρεις τρεπέσθω καὶ πληγὰς, ἀλλὰ παραινείτω, νουθετείτω,
ὡς ἀτελεστέραν λογισμοῖς ἀναπειθέτω, χεῖρας μηδέποτε ἐντεινέτω· πόῤῥω ἐλευθέρας ψυχῆς ταῦτα· ἀλλὰ μηδὲ
ὕβρεις, μηδὲ ὀνείδη, μηδὲ λοιδορίας· ἀλλ' ὡς ἀνοητότερον διακειμένην ῥυθμιζέτω.» In Epistulam ad Ephesios,
Homily 20.
76
«Οἰκέτην μὲν γὰρ φόβῳ τις ἂν καταδῆσαι δυνήσεται, μᾶλλον δὲ οὐδὲ ἐκεῖνον· ταχέως γὰρ ἀποπηδήσας οἰχήσεται·
τὴν δὲ τοῦ βίου κοινωνὸν, τὴν παίδων μητέρα, τὴν πάσης εὐφροσύνης ὑπόθεσιν, οὐ φόβῳ καὶ ἀπειλαῖς δεῖ
καταδεσμεῖν, ἀλλ' ἀγάπῃ καὶ διαθέσει. Ποία γὰρ συζυγία, ὅταν ἡ γυνὴ τὸν ἄνδρα τρέμῃ; ποίας δὲ αὐτὸς ὁ ἀνὴρ
ἀπολαύσεται ἡδονῆς, ὡς δούλῃ συνοικῶν τῇ γυναικὶ, καὶ οὐχ ὡς ἐλευθέρᾳ; Κἂν πάθῃς τι ὑπὲρ αὐτῆς, μὴ ὀνειδίσῃς·
οὐδὲ γὰρ ὁ Χριστὸς τοῦτο ἐποίησε.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
ይሰብካል፡፡ እንዲህ አንዳለ ‹‹ሚስት አካልህ ስለሆነች ክፉ ነገሮች የምታደርግባት ከሆነ የራስህን አካል ባለማክበርህ ትዋረዳለህ
(ታፍራለህ)››77 በሌላም ቦታ እንዲህ አንዳለ ‹‹የራሱን አካል (ራሱን) የሚጠላ ሰው የለም››፡፡78

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንዳንዴ የሚስቶች ጸባይ ከአቅም በላይ ቢሆን ስንኳ እንዲታገሷቸው» ሁሌም በመልካም መንገድ
እንዲቀርቧቸው ለባሎች የተናገረ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ከእግዚብሔር የተሰጣቸው ሓላፊነት መሆኑን ጭምር እንጂ፤ እንዲህ
አንዳለ ‹‹ስለ ማንነቷ ብለህ ከምትወዳት የበለጠ ስለ ክርስቶስ ብለህ ውደዳት››79 በተመሳሳይም ፈርሃ እግዚአብሔር ያለው ባል
ሚስቱን እንደሚወድ ባለ ፍቅር ባሎች ሚስቶቻቸውን ባይወዱ ስንኳ ሚስቶች ግን ባሎቻቸውን ከመውደድና ከማክበር
አንዳይከለከሉ ያዛል፡፡80 ይሄም በሁለቱም በኩል እጅግ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በትዳር ላይ ሳሉ ጉድለት ወይም መቀያየም
ሊኖር ስለሚችል አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ባለመፍረድ በትዳር ሕይወታቸው ለእግዚአብሔር ያለባቸውን ሓላፊነት ሟሟላት
ላይ ማተኮርአለባቸውና ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባልና ሚስት አብረው መቀጠል በፍጹም የማይችሉ እንደሆነ በይሉኝታ ታስረው ከመቆየት ቢለያዩ
አንደሚመርጥም አንዲህ በማለት ያስረዳል፡-

ላገቡ ሰዎች ክርስቶስ ያዘዘው ነገር ምንድነው? ሚስት ከባሏ እንዳትለይ ከተለየች ግን ሳታገባ እንድትኖር ወይም ከባሏ
አንድትታረቅ ነው፡፡፡ በተራክቦ ካለመስማማት እና በሌሎች ተራ ምክንያቶች እንደገናም አንዳቸው ለአንዳቸው ክፉ
ከመሆን የተነሣ ትዳሮች ይፈርሳሉ፤ እንዲህ ዓይነት ነገር ባይፈጠር መልካም ነው ከተፈጠረ ግን ሴቷ ሌላ ባል
አንዳይኖራት ትዳሩ ፈርሶም ቢሆን በአንድ ቤት አብራው ባትኖርም ስንኳ ባሏን ሳትፈታ ትኑር ፡፡81

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መለያየትን ላለማበረታታት ይጥራል ምክንያቱም እግዚአብሔር አንድ ያደረጋቸውን ሁለቱን ክፋዮች
መለያየት አግባብ አይደለምና፡፡ ነገር ግን አብሮነታቸው በሁለቱ መካከል ጠላትነትን እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ተለያይተው
ቢኖሩ ይመርጣል፡፡ ይሄን ሲያደርጉ ግን ወደፊት ለመታረቅ በር ይከፈት ዘንድ ሳያገቡ መቆየት አንዳለባቸው ይመክራል፡፡82
ይሄን የመከረው ግን እርሱ ገንዘብ ካደረገው ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ በመነሣት አንጂ ሁሉን የሚገዛ ሕግ ለመሥራት እንዳይደለ
መታወቅ አለበት፡፡

77
«Ἀλλ' ὅταν ἀκούῃς φόβον, ἐλευθέρᾳ προσήκοντα φόβον ἀπαίτει, μὴ καθὼς παρὰ δούλης· σῶμα γάρ ἐστι σόν· ἂν
γὰρ τοῦτο ποιήσῃς, σαυτὸν καθυβρίζεις, τὸ σῶμα ἀτιμάζων τὸ σόν.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation
from Schaff, NPNF1-13, 275.
78
«Οὐδεὶς γάρ ποτε τὴν ἑαυτοῦ σάρκα ἐμίσησεν.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.
79
«Μὴ δι' ἐκείνην τοίνυν τοσοῦτον, ὅσον διὰ τὸν Χριστὸν αὐτὴν ἀγαπᾷν.» In Epistulam ad Ephesios, Homily
20.Translation in Schaff, NPNF1-13, 277.
80
«Τί οὖν, ἂν μὴ φοβῆται, φησὶν, ἡ γυνή; Σὺ ἀγάπα, τὸ σαυτοῦ πλήρου.Καὶ γὰρ ἂν τὰ παρὰ τῶν ἄλλων μὴ ἕπηται, τὰ
παρ' ἡμῶν ἕπεσθαι δεῖ. Οἷόν τι λέγω· Ὑποτασσόμενοι, φησὶν, ἀλλήλοις ἐν φόβῳ Χριστοῦ. Τί οὖν, ἂν ὁ ἕτερος μὴ
ὑποτάσσηται; Σὺ πείθου τῷ νόμῳ τοῦ Θεοῦ. Οὕτω δὴ καὶ ἐνταῦθα· ἡ γοῦν γυνὴ κἂν μὴ ἀγαπᾶται, ὅμως φοβείσθω,
ἵνα μηδὲν ᾖ παρ' αὐτῇ γεγονός· ὅ τε ἀνὴρ, ἂν μὴ φοβῆται ἡ γυνὴ, ὅμως ἀγαπάτω, ἵνα μηδὲν αὐτὸς ὑστερῇ· ἕκαστος
γὰρ τὸ ἴδιον ἀπέλαβεν.» In Epistulam ad Ephesios, Homily 20.Translation in Schaff, NPNF1-13, 274.
81
«Τί οὖν ἐστιν, ὃ τοῖς γεγαμηκόσι παρήγγειλεν ὁ Κύριος, Γυναῖκα ἀπὸ ἀνδρὸς μὴ χωρισθῆναι; ἐὰν δὲ καὶ χωρισθῇ,
μενέτω ἄγαμος, ἢ τῷ ἀνδρὶ καταλλαγήτω· καὶ ἄνδρα γυναῖκα μὴ ἀφιέναι; Ἐπειδὴ γὰρ καὶ δι' ἐγκράτειαν καὶ δι' ἄλλας
προφάσεις καὶ μικροψυχίας γίνεσθαι διαιρέσεις συνέβαινε, βέλτιον μὲν μηδὲ γενέσθαι τὴν ἀρχὴν, φησίν· εἰ δὲ ἄρα
καὶ γένοιτο, μενέτω ἡ γυνὴ μετὰ τοῦ ἀνδρὸς, εἰ καὶ μὴ τῇ μίξει, ἀλλὰ τῷ μηδένα ἕτερον παρεισαγαγεῖν ἄνδρα.» In
Epistulam i ad Corinthios, Homily 19.Translation in Schaff, NPNF1-12, 188.
82
ጥንዶቹ ክርስቶስንና ቤተክርስቲያንን ወደ መምሰል ጸባያቸውን ከለወጡ ዕርቅ ሊመጣ እንደሚችል የታወቀ ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊ መንገድ የሚሆን ዕርቅ
ደግሞ ኃጢአት የሆነውን ፍቺን የሚያርቅ ብቻ ሳይሆን የላቀ ትሕትናን (ችግርንና ስሕተትን አምኖ መቀበልን) ፣ መልካምነትንና ተግባቦትን በጥንዶቹ መሀል
የሚያመጣና አንዳቸው ለአንዳቸው የተሻለ እንክብካቤን እንዲችሩ የሚያደርግ ውሕደትን የሚያመጣ ነው፡፡
በእኛ ዘመን ያለው አንድምታ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች ወንድና ሴት በመንፈሳዊ እይታ እኩል እንደሆኑና ትዳር ማለት የመሥዋዕትነት ፍቅር
እንደሆነ በግልጽ ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን እንደተገለጸው በኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ የዚህ ትምህርት አረዳድ በታሪካዊ፣ ማኅበራዊ፡
ባህላዊና ግላዊ ምክንያተቶች የተዛባ ሆኖ ቆቷል፡፡ እነዚህ በአጽንኦት የተሰጡ ሐዋርያዊ ትምህርቶች ይህንን የተዛባና የተሳሳተ
አረዳድ ለማስተካከልና ሌሎች ማኅበራዊና ባህላዊ የሆኑ ጎጂ ጠባያትን ለማረም ሊረዱ ይችላሉ፡፡83

በስብከቶቹ ላይ እንደተገለጸው በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ወንድና ሴት በተመሳሳይ ክብርና አምሳል የተፈጠሩና ከመጀመርያውም
አንድ የነበሩ ናቸው፡፡ ይሄ አንድነትም በኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ መልሶ ተገኝቷል፡፡ በባለትዳሮቹ መካከል ስምምነት እንዲኖር ያኽል
የሥልጣን ተዋረድ መኖር አንዳለበት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያሳስባል፡፡ ባል እንደ ራስ ሚስት ደግሞ እንደአካል እንዲያገለግሉ
አድርጎ መግለጹም እርስ በእርስ መደጋገፍ አንዳለባቸው፤ አንዳቸው አንዳቸውንም እንዳይጠሉና እንዳይጎዱ አጽንኦት ለመስጠት
ካለው ፍላጎት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አስተምህሮ ወንድ በመለኮታዊው አሠራር የበላይ ተደርጓል የሚለውን የተሳሳተ አረዳድ
ለማስወገድና የሴቶችን ክብር ለማስጠበቅ ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የትዳር ሕይወት ላይ ላለ አብዛኛውን ሓላፊነት ለሴቶች
ለሚያሸክም ጾታ ተኮር የሓላፊነት ክፍፍል መልስ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ባልና ሚስት አንድ አካል በመሆናቸው የሕይወት
ሸክማቸውን በጋራ ሊሸከሙት አንደሚገባ ያስተምራልና ነው፡፡

ከዚህም ባለፈ ሚስቶቻቸው ላይ ኃይልና ጉልበትን የሚጠቀሙ ባሎችን በግልጽ ይገስጻል፡፡ ባል የገዛ ሰውነቱን (ሚስቱን)
የሚጠላ ከሆነ አብሮ ጠፊ እንደሆነ ገልጧል፡፡ ባሎች ከሚስቶቻቸው አክብሮትን ለማግኘት ቀጣይነት ያለው መልካም የሆነና
አሳቢነት ያልተለየው ፍቅር መለገስ አለባቸው ይላል፡፡ በዚህም ጥሩ ስምምነት ያለበትና በሁለቱም በኩል አስደሳች የሆነ
ግንኙነት ይኖራቸዋል ይላል፡፡ ይህ ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ ባልነት ማለት መንፈሳዊ መሪነትና ራስን አሳልፎ መስጠት ማለት
አንደሆነ በማስረዳት የሴቶችን ጥቃት ለማስቆም ይረዳል፡፡ በሌላ በኩል በትዳር ውስጥ ስለሚኖር ተራክቦ ባስረዳበት ትምህርቱ
በሁለቱም ፈቃድና ፍላጎት መሆን እንዳለበት አጽንኦት መስጠቱ እንደ ትዳር ውስጥ እንዳለ አስገድዶ መድፈር (ባል ያለሚስት
ፍላጎት በጉልበት ቢገናኛት)፣ ከመጠን ያለፈ የተራክቦ ፍላጎት፣ ወይም ሌሎች የፍትወት ስሜት ማርኪያ መንገዶች የባለትዳሮቹን
ሰሜት፣ ክብርና ጤንነት በተጨማሪም የትዳሩን ጤንነት ሊጎዱት ስለሚችሉ ነው፡፡

በመጨረሻም ከገጠሙት ተሞክሮዎች በመነሣት በትዳር ሕይወት ስለሚፈጠር ችግር በጥልቀት ሲመክር በትዳር ውስጥ
መቻቻል መኖር እንዳለበት ነገር ግን ትዳሩ በሁለቱ መካከል ጠላትነትን እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ሴቷ ከክፉ ባሏ ጋር ቤተሰቧ
አንዳይበተን ብቻ ስትል አብራው መኖሯ በምንም መልክ ተቀባይነት የለውም፡፡ የዚህም ምክንያት የእርሷም ፣ የባሏም
የልጆቻቸውም መንፈሳዊ ዕድገት በዚህ ትዳር ውስጥ በመገደቡ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ይሄ በተለይ ለቤተሰባቸው ወይም
ለትዳራቸው ቅድሚያ በመስጠት ጎጂ የሆኑ የትዳር ጥቃቶችን ለሚያስተናግዱ ኦርቶዶክሳዊ ሴቶች ወሳኝ መልእክት ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሴቶች ከእንዲህ ዓይነት ትዳር ተለይተው ለብቻቸው ሳያገቡ መኖርን መምከሩ ለአንዳንድ ሴቶች
መልካም ተግባራዊ አማራጭ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም የሴቶች ይሄንን እርምጃ መውሰድ ባሎችን ክፉ ጠባያቸውን አርመው
ትዳራቸውን ለማስተካከልና ወደቀደመ ሕይወታቸው ለመመለስ እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በእርግጥ ፍቺውን
ከሴትነቷ ጋር የተያያዙና ንብረት ነክ የሆኑ ጉዳዮች ሊያጓትቱት ይችሉ ይሆናል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጊዜ አንድ ዓይነት መላ
ወይም መንገድ ብቻ ላይኖር ይችላል፡፡ ምንም ስንኳ ውሳኔው የሴቷ ቢሆንም የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክሮች የውሳኔ
ዕድሎቿን ለማስፋት ይረዳሉ፡፡

ሦስት ሁኔታዎች ግን መታወቅ አለባቸው፡-

83
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜዎች (ትምህርቶች) ጸባይንና የተሳሳቱ አረዳዶችን ለመቀየር ያላቸውን አቅም ከ Gassin, “Eastern Orthodox
Christianity,” 2015 ይመልከቱ፡፡
1) ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ በቤተክርስቲያን ትምህርት ይታነጻል ማለት እንዳልሆነ ምክያቱም ሁሉም ተመሳሳይ መንፈሳዊ
ዕውቀትና አረዳድ ስለማይኖረው

2) እነዚህ ትምህርቶች የኃይለኛነት ጸባይን ሊፈጥሩ የሚችሉ ከአካላዊ ዕድገት፣ ከሥነ ልቡና እና ከአካባቢያዊ ተጽእኖ
የሚመጡ ምክንያቶችን በተመለከተ የተሟላ አስተያየት መስጠት ስለማይችሉ፤ በሥነ-ልቦና ሕክምና መታገዝ እንደሚችሉ
ማወቅ84

3) አንዳንድ መምህራን ስለ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ፣ ስለ የትዳር ጥቃትና ለሕፃናት ስለሚሰጥ መንፈሳዊ ምክር በቂ ዕውቀት
ስለማይኖራቸው እነዚህን ትምህርቶች ለምእመናኑ በተገቢው ሁኔታ ማድረስ ላይ ችግር ሊያጋጥም ስለሚችል የመምህራኑንም
ዕውቀትና አረዳድ ማማከል ያስፈልጋል85፡፡

ዋቢ

ከኦርጅናሉ ግሪክ ተወስደው ለማጣቀሻነት የዋሉ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስብከቶች

Chrysostom, John. De Virginitate, Index of /pgm/PG_Migne/John Chrysostom_PG 47-64.


Accessed December 13, 2016.
http://khazarzar.skeptik.net/pgm/PG_Migne/John%20Chrysostom_PG%2047-64/
Chrysostom, John.In epistulam ad Colossenses, Index of /pgm/PG_Migne/John Chrysostom_PG
47-64.Accessed December 13, 2016.
http://khazarzar.skeptik.net/pgm/PG_Migne/John%20Chrysostom_PG%2047-64/
Chrysostom, John. In epistulam ad Corinthios, Index of /pgm/PG_Migne/John Chrysostom_PG
47-64.Accessed December 13, 2016.
http://khazarzar.skeptik.net/pgm/PG_Migne/John%20Chrysostom_PG%2047-64/
Chrysostom, John.In epistulam ad Ephesios, Index of /pgm/PG_Migne/John Chrysostom_PG
47-64.Accessed December 13, 2016.
http://khazarzar.skeptik.net/pgm/PG_Migne/John%20Chrysostom_PG%2047-64/
Chrysostom, John.In epistulam ad Hebraeos, Index of /pgm/PG_Migne/John Chrysostom_PG
47-64.Accessed December 13, 2016.
http://khazarzar.skeptik.net/pgm/PG_Migne/John%20Chrysostom_PG%2047-64/
Chrysostom, John.In Genesim Sermones, Index of /pgm/PG_Migne/John Chrysostom_PG 47-
64. Accessed December 13, 2016.
http://khazarzar.skeptik.net/pgm/PG_Migne/John%20Chrysostom_PG%2047-64/

84
James Gilligan, Violence: Reflections on our Deadliest Epidemic (London: Jessica Kingsley Publishers, 1999); Donald
Dutton, The Abusive Personality: Violence and Control in Intimate Relationships (New York: Guilford Publications,
2007); Linda Mills, “Shame and Intimate Abuse: The Critical Missing Link between Cause and Cure,”Children and Youth
Services Review 30 (2008): 631–63.
85
በኦርቶዶክስ ትውፊት አማኞች ኃጢአታቸውን የሚናዝዛቸው የንስሓ አባት በነፍስ ወከፍ ይኖራቸዋል፡፡ የንስሓ አባት በጥንዶች ሕይወት ውስጥም
በጥልቀት ተሳታፊ ሲሆን ችግሮች በሚኖሩበትም ጊዜ ጥንዶቹ ቀድመው የሚያሳውቁት ለእርሱ ነው፡፡
Chrysostom, John. In Genesim (sermo 3), Index of /pgm/PG_Migne/John Chrysostom_PG 47-
64.Accessed March 15, 2018.
http://khazarzar.skeptik.net/pgm/PG_Migne/John%20Chrysostom_PG%2047-
64/In%20Genesim%20sermo%203

የእንግሊዝኛ ማጣቀሻዎች

Miller, P. Cox. Women in Early Christianity: Translations from Greek Texts, Catholic University
of America Press, 2012.
Roth, Catharine and David Anderson. St. John Chrysostom: On Marriage and Family Life, St.
Vladimir’s Seminary Press, 1997.
Schaff, Philip, ed. NPNF1-09, St. Chrysostom: On the Priesthood; Ascetic Treatises; Select
Homilies and Letters; Homilies on the Statutes, Christian Classics Ethereal Library.
Accessed April 3, 2016. www.ccel.org/ccel/schaff/npnf109.html
Schaff, Philip, ed. NPNF1-12.Saint Chrysostom: Homilies on the Epistles of Paul to the
Corinthians. Christian Classics Ethereal Library. Accessed April 3, 2016.
www.ccel.org/ccel/schaff/npnf109.html
Schaff, Philip, ed. NPNF1-13 Saint Chrysostom: Homilies on Galatians, Ephesians, Philippians,
Colossians, Thessalonians, Timothy, Titus, and Philemon. Christian Classics Ethereal
Library. Accessed April 2, 2016. www.ccel.org/ccel/schaff/npnf109.html
Schaff, Philip, ed. NPNF1-14, Saint Chrysostom: Homilies on the Gospel of St. John and the Epistle
to the Hebrews, Christian Classics Ethereal Library. Accessed April 2, 2016.
www.ccel.org/ccel/schaff/npnf114.html

የግሪክ ቋንቋ ማጣቀሻዎች

Βενέδικτος Ιερομόναχος Αγειορίτης. Αγίου Ιωάννου του Χρυσοστόμου. Χρυσοστομικός Άμβων


Γ’: Ο Γάμος, η Οικογένεια και τα Προβλήματά τους. Νέα Σκήτη Αγίου Όρους:Συνοδία
Σπυρίδωνος Ιερομονάχου, 2014.
Λέκκος, Π. Ευάγγελος. Αγίου Ιωάννου του Χρυσοστόμου.Οι Πρωτόπλαστοι (Γενέσεως 1,26-
2,20). Αθήνα: Εκδόσεις Λύχνος EΠΕ, 2004.
Πατάκης, Α. Σρέφανος and Νικόλαος Ε. Τζιράκης. Λεξικό Ρημάτων Αρχαίας Ελληνικής. Αθήνα:
Εκδόσεις Πατάκη, 1973.
Χαρώνης, Δ. Βασίλειος and Ουρανία Α. Λαναρά. Παιδαγωγική Ανθρωπολογία Ιωάννου
Χρυσοστόμου, Αθήνα: Εκδοτικός Οίκος Ελευθερίου Μερετάκη ‘Τό Βυζάντιο’, 1994.

You might also like