[go: up one dir, main page]

Jump to content

I

ከውክፔዲያ
የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

I / iላቲን አልፋቤት ዘጠኝኛው ፊደል ነው። በእንግሊዝኛ የፊደሉ ስም አጠራር /አይ/ ሲሆን፣ ይህ ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅን ያንጸባርቃል። ባብዛኛው ቋንቋዎች ግን በተለመደው የአናባቢ «ኢ» ን ድምጽ ኃይል ይወክላል።

ግብፅኛ
ቅድመ ሴማዊ
ዮድ
የፊንቄ ጽሕፈት
ዮድ
የግሪክ ጽሕፈት
ኢዮታ
ኤትሩስካዊ
I
ላቲን
I
D36

የ«I» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዮድ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የክንድ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ የግብጽኛ ተናባቢ ድምጽ ምልክቶች በሚል አጠራር ለድምጹ «ዐ» ይጠቀም ነበር። በሴማውያን ፊደል ግን ለ«ይ» ይጠቀም ጀመር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።

በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ዮድ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ይ») ሲሆን በግሪክ አልፋቤት ደግሞ እንደ አናናቢው ኢዮታ ለ «ኢ» ተጠቀመ።

የላቲን I ከዚህ ሲሆን ደግሞ ለ«ይ»፣ «ኢ» እና ለሮማይስጡ ቁጥር ፩ ተጠቀመ። በቃል መጨረሻ ሲደረብ እንደ -ii ሲጻፍ፣ ቅርጹ እንደ -ij ይምሰል ጀመር። ከ1516 ዓ.ም. ጀምሮ ቅርጹ «J» ለተናባቢው «ይ» እና ቅርጹ «I» ለአናባቢው «ኢ» ይለያዩ ጀመር።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «» («የመን») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ዮድ» ስለ መጣ፣ የላቲን «I» ዘመድ ሊባል ይችላል።

«i» ደግሞ በሥነ ቁጥር በተመከለተው የአቅጣጫ ቁጥር ሊወክል ይችላል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ I የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።