አዝማሪ ቋንቋ
Appearance
የአዝማሪ ቋንቋ የሚሰኘው አዝማሪወች እርስ በርሳቸው የሚግባቡበትና ሌሎችን የሚያገሉበት የምስጢር ቋንቋ ነው። ይህን የሚያደርጉት ፡
- የአንድን ቃል ፊደላት በመቀየር
- ፊደላትን በመደጋገም
- አዲስ ፊደል ቃሉ ውስጥ በመጨመር
- የቃላቱን አናባቢወች ሙሉ በሙሉ በመገልበጥ
- የቃላቱን አናባቢወች በተለያየ መልኩ (2-3-1 ወይም 3-2-1 ወይም 1-3-2 በመገልበጥ)
ምሳሌ፡
እንባ --> አናንባ
ደስ አለኝ --> ደሰሰና ሞሰኝ
ሳር --> ስርንስር
ፍሬ --> ፍርንፍር
ቀዳ --> ቀረዳ
በለጠ --> በለነጠ
በላ --> ላበ
ተዝናና --> ናናዝተ
ተኛ --> ኘታ
መብት --> ተምብ (3-1-2)
ወደቀ --> ደወቀ (2-1-3)
- ^ Wolf Leslau, An Ethiopian Minstrels' Argot, Journal of the American Oriental Society Vol. 72, No. 3 (Jul. - Sep., 1952), pp. 102-109