ማሪ
Appearance
ማሪ (ተል-ሐሪሪ) | |
---|---|
የማሪ ፍርስራሽ | |
ሥፍራ | |
ዘመን | 2350-1673 ዓክልበ. |
ዘመናዊ አገር | ሶርያ |
ጥንታዊ አገር | ማርቱ |
ማሪ የመስጴጦምያ ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው በአረብኛ ተል ሐሪሪ ተብሎ ብዙ ጽላቶች የተገኙበት ፍርስራሹ በዘመናዊው አገር ሶርያ ውስጥ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይገኛል።
የማሪ ነገሥታት
ከማሪ ጽላቶች እንዲሁም ከኤብላ ጽላቶች ከተገኘው በርካታ መረጃ የማሪ ነገሥታት ዘመኖች ሊታወቅ ይቻላል።
መጀመርያ የሚታወቀው የማሪ ንጉሥ በኡር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ዘመን (2345-2314 ዓክልበ. ግ.) የነገሠው ጋንሱድ ይመስላል። ጋንሱድ ከመስ-አኔ-ፓዳ ጋር በዚህ ዘመን ንግድ እንዳካሄደው ይታወቃል። ከዚያ በኋላ የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ግዛቱን እስከ ማሪ ድረስ አስፋፋ። በኤአናቱም መሞት (2195 ዓክልበ. ግ.) ማሪ እንደገና ነጻ መንግሥት ሆነ።
- ኢኩን-ሳማሽ 2195 ዓክልበ. ግ.
- ኢኩን-ሳማጋን
- ላምጊ-ማሪ (ኢሽኪ-ማሪ)
- አኑቡ
- ሳዑሙ
- ኢቱፕ-ኢሻር
- ኢብሉል-ኢል 2127?-2115 ዓክልበ. ግድም - «የማሪና የአሹር ንጉሥ» ተባለ፤ ከርሱ በኋላ ግን አሦር ነጻ ሆነ።
- ኒዚ 2115-2114 ዓክልበ. ግድም
- ኤና-ዳጋን 2114-2112 ዓክልበ. ግድም - የኤብላ ንጉሥ ኢሻር-ዳሙ የሾመ አለቃ ነበረ።
- ኢኩን-ኢሻር 2112 ዓክልበ. ግድም
- ሒዳዓር 2112-2077 ዓክልበ. ግድም - ከ2107-2100 ዓክልበ. ግ. ደግሞ የሱመር (ኒፑር) ንጉሥ እንደ ሆነ ይመስላል።
- ኢሽቂ-ማሪ 2077-2068 ዓክልበ. ግድም
የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ማሪን ያጠፋው በኢሽቂ-ማሪ ፱ኛው ዓመት ይመስላል። ከዚያ በአካድ መንግሥት ዘመን አለቃው ኢዲዲሽ በማሪ ላይ ተሾመ። ከእርሱ በታች «ሻካናኩ» (ሻለቆቹ) የተባለው ኟሪ ወገን በማሪ ተነሣ። እነርሱም፦
- ሱ-ዳጋን 2068-2063
- ኢሽማህ-ዳጋን 2063-2018
- ኑር-መር 2018-2013
- ኢሽዱብ-ኤል 2013-2002
- ኢሽኩን-አዱ 2002-1994
- አፒል-ኪን 1994-1959 - ከሰነዶች ዘመኑ የኡቱ-ኸጛልና የኡር-ናሙ ዘመናት እንደ ጠቀለለ ይረጋገጣል።
- ኢዲን-ኢሉም 1959-1954
- ኢሉም-ኢሻር 1954-1942
- ቱራም-ዳጋን 1942-1922
- ፑዙር-ኤሽታር 1922-1897 - የፑዙር-ኤሽታር ፩ኛው ዓመት የሹልጊ ፵፬ኛው ዓመት መሆኑን ይታወቃል።
- ሒትላል-ኤራ 1897-1890
- ሐኑን-ዳጋን 1890-1882
- ኢሲ-ዳጋን 1882-1876?
- ኢቱር-? 1876-1870 ?
- አመር-ኑኑ 1870- 1864 ?
- ቴር-ዳጋን 1864-1856 ?
- ዳጋን-? 1856-1850 ?
...
- ያጊት-ሊም ?-1723
- ያኽዱን-ሊም 1720-1707
- ሱሙ-ያማን 1707-1705
- 1 ሻምሺ-አዳድ (በአሦር መንግሥት) 1705-1694
- ያስማህ-አዳድ (1694-1687)
- ዝምሪ-ሊም 1687-1673
በ1673 ዓክልበ. ማሪ ለባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ወደቀ።
-
ኢኩን-ሳማጋን?
-
ኢዲን-ኢሉም
-
ፑዙር-ኤሽታር